በተያዘው በጀት ዓመት ከ96 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ለክስ ተዳርገዋል፡፡በመዲናዋ የትራፊክ መብራትን የሚጥሱ አሽከርካሪዎች ቁጥር ተበራክቷል ተባለ፡፡ በያዝነው አመት አጋማሽ 96 ሺ አ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/VIcMvcECEgLI4d2jnTXJjWX0YBgaMiY26RRzNq5vlttrIrhZU3P5WgNpHWGyWVAcDGYTWy9vp8VfEPWSk_CmnWAwIgJr56rrOncJuZICyMlWWXaRIoh6BhaVTZ5TFinF5rLeQyfD8ceZU54tP0YzixFiaFIQeLsB63U1ReNMJupW0ZLnEe_dMdJWbISIYZ2TMsK5e4A6iEP_3xwgFAf0J0ZsxpH2JsM5JgIWazyvM8LXgRJLi-_oPOKouvOiqIIG1crhZCM8xUfr05eeSmrrIhJHwUUent4lpqc3oD6Ep7VZcy2WrYW84L2H5DBpj4CB1eoYfL9xF0JeI9DwmpHfmg.jpg

በተያዘው በጀት ዓመት ከ96 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ለክስ ተዳርገዋል፡፡

በመዲናዋ የትራፊክ መብራትን የሚጥሱ አሽከርካሪዎች ቁጥር ተበራክቷል ተባለ፡፡

በያዝነው አመት አጋማሽ 96 ሺ አንድ መቶ 75 አሽከርካሪዎች ቀይ የትራፊክ መብራት ጥሰው በማሽከርከራቸው ተሰከዋል፡፡

በአዲስ አበባ ፓሊስ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሙያና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳስታወቁት በመዲናዋ የትራፊክ ደንብን በመተላፍ የትራፊክ መብራትን የሚጥሱ አሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ እየሆነ መቷል።

አጠቃላይ የትራንስፓርት እና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በወጣው ደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት ደንቡን ተላልፈው የተገኙ አሸከርካሪዎች እንደሚቀጡ ተናግረዋል፡፡

አሽከርካዎች የትራፊክ መብራቶችን አክብሮ በመንቀሳቀስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ሀላፊነታቸውን እና ድርሻቸውን እንዲወጡ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ጀምሮ ሰፊ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ኢንስፔክተር ሰለሞን ተናግረዋል።

የትራፊክ አደጋ ምጣኔ ሃብታዊ ፤ማህበራዊ እና በአጠቃላይ በሃገሪቱ ላይ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዳለው ስለሚታወቅ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

በሐመረ ፍሬው

የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply