You are currently viewing በተደረገው ሀገራዊ ጥሪ መሰረት ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን ወደ ውቢቱ ባህርዳር እንዲመጡ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህ…

በተደረገው ሀገራዊ ጥሪ መሰረት ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን ወደ ውቢቱ ባህርዳር እንዲመጡ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህ…

በተደረገው ሀገራዊ ጥሪ መሰረት ኢትዮዽያውያንና ትውልደ ኢትዮዽያውያን ወደ ውቢቱ ባህርዳር እንዲመጡ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሀገራችን ኢትዮዽያ ያለውን እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብት ለማውደም የተሰለፉ የውስጥና የውጭ አፍራሽ ኃይሎችን የጥፋት ሴራ በመበጣጠስ የነበረ የጀግንነት ታሪካችንን በማስቀጠል በኩል ሁሉም ኢትዮዽያዊና ትውልደ ኢትዮዽያዊ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ባህርዳር ከተማም በርካታ እንግዶችን ለመቀበል የራሷን ተገቢ ዝግጅት ማድረጓን አስመልክቶ የከተማዋ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ መግለጫ ሰጥተዋል። እንደ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገለፃ ከተማችን ባህርዳር ባለብዙ ገፀ-በረከት ከተማ በመሆኗ በርካታ የቱሪስትና ኢንቨስትመንት ፍሰቶችን እያስተናገደች የምትገኝ ውብ ፣ምቹና ፅዱ ከተማ ናት ብለዋል። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ወራሪውና አሸባሪው የትግራይ አፍራሽ ቡድን የህዝብ ሰላምና ልማት ጠላት በመሆን በንፁሃን ህይወት ፣ሀብት ንበረት ላይ አስከፊ የሆነ ጥፋት እያደረሰ ቢሆንም በህዝቦች የተባበረ ክንድና በጀግናው ጥምር ጦር የበረታ ትግል እየተደመሰሰ በሚገኝበት ወቅት ላይ ዲያስፖራው ወደ ሀገር ቤት መጠራቱ ለድሉ ስኬታማ ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የባህርዳር ከተማ እንግዶችን ለመቀበል ከባለ ሀብቱ ፣ከአስጎብኝ ማህበራት እና ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት እንግዶቻችን በቆይታቸው ስለሚያደርጓቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አስፈለጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ያጠናቀቁ መሆኑንም ገልፀዋል። ከንቲባ ዶ/ር ድረስ አያይዘውም በባህርዳርና አካባቢው የሚገኙ የቱሪስት ፣የኢንቨስትመንት እና ሌሎች የሰላምና የልማት ጉዳዮችን በማመቻቸት ከታህሳስ 25/2014 ዓ/ም ጀምሮ ለእንግዶቹ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ የተዘጋጁ መሆኑንም ተናግረዋል። በማስቀጠልም ከጥር 01/2014 እስከ 05/2014 ድርስ እንግዶቻችን በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት አማራጮችን የያዙ የአውደ ጥናት መርሃ ግብሮችን በማከናወን ዲያስፖራው ያለውን ሀብትም ሆነ እውቀት በዚህች ውብ ከተማ እንዲያውል የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አማራጮች ይቀርባሉ ብለዋል። በአጠቃላይ መላው ኢትዮዽያዊና ትውልደ ኢትዮዽያዊ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ተቀናጅቶ እና በአንድ ልብ በመቆሞ በሀገራችንም ሆነ በከተማችን እያከናወንን ላለው የልማት ፣የሰላምና ዲሞክራሲ ግንባታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ለማሳረፍ የሚቋምጡ አፍራሽ ኃይሎችን ድል በመንሳት የቀደመ ክብራችንን የምናስቀጥልበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ያለው የባህር ዳር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply