በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የገለፀው አንጋፋው አርቲስት ቴዲ አፍሮ መንግስት የዜጎችን…

በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የገለፀው አንጋፋው አርቲስት ቴዲ አፍሮ መንግስት የዜጎችን…

በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የገለፀው አንጋፋው አርቲስት ቴዲ አፍሮ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ታዋቂውና አንጋፋው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገጹ እንዳሰፈረው በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች አሳሳቢ መሆናቸውን ጠቅሷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መንገድ ተስፋፍተው መቀጠላቸውን ተያይዞ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበትና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ መንግስታዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል። በተጨማሪምመንግስት መሰል ጥቃቶች ዳግመኛ እንዳይፈፀሙ የሚጠበቅበትን የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እንዲሰራ በጥብቅ ለማሳሰብ እወዳለሁ ብሏል አርቲስት ቴዲ አፍሮ። በመጨረሻም በዚህ አጋጣሚም በእነዚህ ጥቃቶች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እንዲሆንላቸው ከልብ እመኛለሁ ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply