በተጋጋለው የቶፕ 4 ፉክክር ወደኋላ የቀረው ቼልሲ በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎው ላቅ ያለ ቢሆንም እስካሁን የተንገራገጨ የሊግ ጉዞ እየከወነ ይገኛል በዛሬ ምሽትም በሜዳው ስታንፎርድ ብሪጅ ለዋን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/CY3UwiL1UJWiiX8iCzi6wEqfktKKL7cCrgQcfgCLQoLvpjMIXaFRQdAQdQ_SKSvisZ7dib7pppQHZFgv1rObcmsaE8puEIZYls9puwnz5tX_mQ5iHFNhdrU5JJxJYSNybcVGmOETUDtQULjLzmiAfEaZhYF5ZZd3IdTuGdY7TRaaRH-siKi5XUybG5zQr6KjxCp8rHVsqxd5lSIAwoLD5_ebOCYuWxWqVUu_JoAQeoZlvvrcIqMfWu8UpLBT72Xi8OZIBxjKcaIdSNHY6qtr3rT8XnFTkWs_7JXt_KkbJQ89dMw8A6rCvZkgC0kj9868LCoTVguG9z1wQsoHpHMVvA.jpg

በተጋጋለው የቶፕ 4 ፉክክር ወደኋላ የቀረው ቼልሲ በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎው ላቅ ያለ ቢሆንም እስካሁን የተንገራገጨ የሊግ ጉዞ እየከወነ ይገኛል በዛሬ ምሽትም በሜዳው ስታንፎርድ ብሪጅ ለዋንጫ ተገማቹን ሆኖም ተደጋጋሚ ነጥብ በመጣል ለመድፈኞቹ የናፈቁትን የሊግ የበላይነት እንዲያሳኩ መንገድ እየጠረገ ያለውን ማንሲቲን ያስተናግዳል::

ባለፉት አመታት በአሰልጣኝ ቱኸል ስር በተለይ በጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ሲቲን ሲገዳደር ሰንብቷል ሆኖም ቱኸልም ሆኑ አሁን በመንበሩ የተቀመጡት ፖተር የዘንድሮው የባለቤት ልውውጥ ለለንደኑ ተቀማጭ ቡድን ምቾት የነፈገ መስሏል በደረጃ ሰንጠረዡም አጋማሽ ላይ ተቀምጦ የቀጣይ አመት የአውሮፓ ተሳትፎ እንደ ሰማይ ርቆታል ማንሲቲም ቢሆን በገና ሰሞን በለመደው ከፍታ መገኘት አልቻለም ጎል አነፍናፊው ተለምዷዊ ተግባሩን ባያቋርጥም ከኋላ ግን እያፈሰሰ ነጥቦችንን ማንጠባጠብ ቀጥሎበታል ዛሬስ ምን ይጠበቃል?

ሰማያዊዎቹ ድል ቀንቷቸው ከረቱ ምናልባትም ለከተማ ክለባቸው በቀደው በኒውካስትል የጣሉትን ነጥብ መልሰው የሚያገኙ ሲሆን የአምና ሻምፒዮኖቹ ከረቱ የነጥብ ልዩነቱ ወደነበረበት አምስት ይመለስና ቼልሲ ግን ማጣፊያው ያጥረዋል ምን ይጠበቃል ከምሽት 3፡00 ጀምሮ ተገናኝተን የበዓል አዝናኝ ጭውውቶችን ጨምረን እስከ 7፡00 እንዘልቃለን ቀጠሮአችሁ
ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጋር ይሁን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply