You are currently viewing በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አዲስ ርዕደ መሬት ተከስቶ የበርካቶች ህይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ከሁለት ሳምን…

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አዲስ ርዕደ መሬት ተከስቶ የበርካቶች ህይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሁለት ሳምን…

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አዲስ ርዕደ መሬት ተከስቶ የበርካቶች ህይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ ከ47 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። በደቡብ ምስራቃዊ ቱርክየካቲት 13/2015 በደረሱ ሁለት የርዕደ መሬት አደጋዎች በጥቂቱ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። ቱርክን ከሶሪያ በሚያዋስነው ድንበር በተከሰቱት አደጋዎች እስካሁን 294 ሰዎች መቁሰላቸውንም ነው የቱርኮ ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀው። በርዕደ መሬት መለኪያ 6 ነጥብ 4 እና 5 ነጥብ 8 ሆነው በተመዘገቡት አደጋዎች በርካታ ህንፃዎች የፈራረሱ ሲሆን፥ በፍርስራሽ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የማውጣቱ ስራም መቀጠሉ ተገልጿል። ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ምክንያት ከመኖሪያ ህንፃዎች የወጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ግን የሟቾቹ ቁጥር እንዲቀንስ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። ቱርክ የነፍስ አድን ሰራተኞችን በስፋት አሰማርታ ፍርስራሽ ውስጥ የተደበቁ ሰዎችን ለማትረፍ እየተረባረች እንደምትገኝ ቲ አር ቲ ዘግቧል። በቱርክ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፥ ዋሽንግተን ለተጎጂዎቹ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል። በ15 ቀናት በፊት በደረሰው አደጋ በቱርክ ብቻ ከ41 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ ከ380 ሺህ በላይ ህንፃዎች ፈራርሰዋል። ቱርክ ከርዕደ መሬቱ ጋር በተያያዘ የግንባታ ተቋራጮችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀመረች የነፍስ አድን ስራውም መገባደዱን ተከትሎ አንካራ ትኩረቷን ወደ መልሶ ግንባታ ታዞራለች ብለዋል ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን። ከቀጣይ ወር ጀምሮም የ200 ሺህ የመኖሪያ ህንፃዎች ግንባታ ይጀመራል ነው ያሉት። ትናንት የተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ያወደመው ህንፃ ቁጥር ገና ይፋ ባይደረግም የቱርክ መንግስትን የቤትጰስራ ማብዛቱ እንደማይቀር ይታመናል። ቱርክ ርዕደ መሬት የሚቋቋሙ ህንፃዎች እንዲገነቡ የህንፃ ግንባታ ህግ ብታወጣም ተፈፃሚ አለመሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህንፃዎች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል። አንካራ ከወደሙት ህንፃዎች ጋር በተያያዘ 131 የህንፃ ተቋራጮች ላይ የእስር ማዘዣ አውጥታ በቁጥጥር ስር እያዋለች መሆኑን አናዶሉ አስታወሷል ሲል አል ዐይን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply