You are currently viewing በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ሆኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ…

በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ሆኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ…

በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ5 ሺህ በላይ ሆኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ምስራቅ ቱርክ በጋዚያንቴፕ ከሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተዉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በቱርክ ብቻ ከ3,549 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሰኞው አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በከፋ ጉዳት በደረሰባቸው 10 ግዛቶች ዉስጥ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። በ10 ከተሞች ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሀገሪቱ ከ1939 ዓ.ም ወዲህ ባጋጠሟት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በመሬት መንቀጥቀጡ ወደተመቱ አካባቢዎች የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ወዲያውኑ መላኩን ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ከተጎዱት የስምንት ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጽህፈት ቤታቸው መግለጫ አስታውቋል። ፕሬዝዳንቱ አክለዉ አሜሪካ፣ እንግሊዝን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ እርዳታ ላደረጉ 70 ሀገራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ኳታር 10,000 ተንቀሳቃሽ ቤቶችን በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ120 የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጋር ልካለች፡፡ ከ11 ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው ሶሪያ፣ ከ1,602 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 3,500 የሚያህሉ ሰዎች መቁሰላቸውን የሶርያ የመንግስትና ወዶ ገቡ የነጭ ቆብ የረድኤት ተቋም አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሶርያ ሐማ፣ አሌፖ እና ላታኪያ ግዛቶች በርካታ ሕንፃዎችን አውድሟል። የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋዚያንቴፕ ከተማ አቅራቢያ 17.9 ኪ/ሜ ያለው ጥልቀትና በሬክተር ስኬል 7.8 የተለካ አደጋ መድረሱን ይፈ አድርጓል። የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተሰማው በዋና ከተማዋ አንካራ እና በሌሎች የቱርክ ከተሞች እንዲሁም በሰፊው የሀገሪቱ ክልል መሆኑን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። በአደጋው በርካታ ሕንፃዎች የፈረሱ ሲሆን በዲያርባኪር ከተማ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ወድሟል። አንድ እማኝ እንደተናገሩት እኔ ያረፈኩበት ቤት ለ45 ሰከንድ ያህል መንቀጥቀጡን ተናግረዋል። የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካ እንደሆነ ገምተዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ መንቀጥቀጥ አካባቢውን እንደመታ ተናግረዋል። ቱርክ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚደርስባቸው ዞኖች ውስጥ አንዷ ነች። እ.ኤ.አ. በ 1999 በቱርክ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ17,000 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ዘገባው የዳጉ ጆርናል ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply