You are currently viewing በቲሊሊ ማጎሪያ ጣቢያ የሚገኙ 13  የግፍ እስረኞች ለሃምሌ 21 ቀን ተቀጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ  በአማራ ህዝብ ትግል በ…

በቲሊሊ ማጎሪያ ጣቢያ የሚገኙ 13 የግፍ እስረኞች ለሃምሌ 21 ቀን ተቀጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ህዝብ ትግል በ…

በቲሊሊ ማጎሪያ ጣቢያ የሚገኙ 13 የግፍ እስረኞች ለሃምሌ 21 ቀን ተቀጠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ህዝብ ትግል በአብን ውስጥ በአመራርነትና በአባልነት በመሳተፍ የተሻለ አበርክቶት ያላቸው 13 ወጣቶች በጎጃም ቲሊሊ ያለፍትህ ታስረው እንደሚገኙ ተገልጧል። ወጣቶቹ ሃምሌ 19/2014 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርበው ነበር፤ ቀጠሮአቸውም የነበረው በዋስትና ጥያቄያቸው ጉዳይ የክልሉ አቃቢ ህግ አስተያየት እንዲሰጥበት በሚል ነበር። ከሁለት ወራት በላይ በተለያዩ አካባቢዎች በእስር እየተንገላቱ ያሉት እነዚህ የግፍ እስረኞች ለሃምሌ 21/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጧል። በእስር ላይ ከሚገኙት መካከልም:_ 1) አቶ ክንፈመላክ ካሳ_ የአነደድ ወረዳ አብን ሰብሳቢ 2) አቶ አስማማው ሞላ_ የማቻከል ወረዳ ፋኖ አስተባባሪ፣ 3) አቶ ስዩም ይዘንጋው_የቢቡኝ ወረዳ የፋኖ አባል፣ 3) መ/ር እንዳላማው አዲስ_ በማቻከል ወረዳ የመ/ራን ማህበር ሰብሳቢ፣ 4) አቶ ደጀኔ መለሰ_ የማቻከል ንቁ አማራና አክቲቪስት እንደሚገኙበት ታውቋል። በመጨረሻም በህግ ማስከበር ስም የታሰሩ የግፍ እስረኞች አስቸኳይ ፍትህ ያገኙ ዘንድ ሁሉም ድምፅ እንዲሆናቸው ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply