በቲቢ በሽታ የመያዝ መጠንን በ90 በመቶና የመሞት መጠንን በ95 በመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡



በቲቢ በሽታ የመያዝ መጠንን በ90 በመቶና የመሞት መጠንን በ95 በመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና
ቢሮ ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ነዋሪነታቸው በዳባት ወረዳ የሆነው አቶ ፈንታሁን መኳንንት በቲቢ ተይዘው
ታክመው ድነዋል፤ ከሦስት ወራት በላይ ቢታመሙም ምርመራ ሳያደርጉ መቆየታቸውንና ህመሙ ሲብስባቸው ወደ ጤና ተቋም
ሄደው ሲመረመሩ ቲቢ እንደተገኘባቸው ጠቅሰዋል። ፈጥነው ወደ ሕክምና ያልሄዱት በግንዛቤ ማጣት እንደነበርም ተናግረዋል፡፡
አቶ ፈንታሁን እንዳሉት በሕክምና ባለሙያዎች የታዘዘላቸውን መድኃኒት ለስድስት ወራት በትክክል ወስደው መጨረሳቸውንና
አሁን ሙሉ በሙሉ መዳናቸውን በሐኪም እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡
“የጤና ባለሞያዎቹን እንደ እናት፣ ጤና ተቋሙን እንደ ቤቴ ነው የማያቸው፤ ምክራቸውም በጣም ጥሩ ነው” ብለዋል አቶ
ፈንታሁን፡፡
የቲቢ ምልክቶች የታዩበት ሁሉ ፈጥኖ ወደ ሕክምና ተቋም እንዲሄድና በነጻ እንዲታከምም ጠይቀዋል፡፡
በዓለም ለ39ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ24ኛ እና በአማራ ክልል ለዘጠነኛ ጊዜ የሚከበረውን የቲቢ ቀን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ
ፈጠራና የአሰሳ ሥራ መሠራቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ቀኑን በማስመልከት በደብረ ታቦር ከተማ ውይይትና ቲቢን
የመከላከል የአደባባይ ቅስቀሳ ሥራ ተካሂዷል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በቲቢ በሽታ የመያዝ ምጣኔ 140 ከአንድ
መቶ ሺህ ተመርማሪዎችና እና የመሞት ምጣኔ ደግሞ 19 ከአንድ መቶ ሺህ ስለሆነ አሁንም አሳሳቢና ቀጣይ ሥራ የሚጠይቅ
መሆኑንም አሳስበዋል፡፡
የዓለም የቲቢ ቀን በየዓመቱ ሲከበር በሽታው የኅብረተሰብ የጤና ችግር ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለመቀነስ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቢሮው የቲቢ፣ ኤች.አይ.ቪ እና የሥጋ ደዌ በሽታዎች መከላከል ባለሙያ አደባባይ ካሴ እንዳሉት በተያዘው መጋቢት ወር ብቻ
•ከ500 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለ በሽታው ግንዛቤ ተፈጥሯል፤
•ለ54 ሺህ ሰዎች የቲቢ ልየታ ምርመራ ተደርጓል፤
• 1 ሺህ 700 ሰዎች የቲቢ በሽታ ምልክት
ታይቶባቸዋል
• ከ10 የቲቢ ህመምተኞች አንድ መድኃኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ ተገኝቷል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን ያክል የቲቢ በሽታ ከተገኘ በሰፊ ቦታዎችና ሕዝብ ላይ ምርመራው ቢደረግ የበለጠ ሊሆን
እንደሚችል ያስገነዝባል ብለዋል አቶ አደባባይ፡፡
ጤና ቢሮው በቲቢ የመያዝ መጠንን በ90 በመቶ፣ የመሞት መጠንን በ95 በመቶ ለመቀነስና በቲቢ ምክንያት የሚፈጠሩ
ወጪዎችን ዜሮ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ቲቢን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ንቁ ተሳታፊና እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ – ከደብረ ታቦር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m




Previous articleብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ትክክለኛ የአማርኛ ቋንቋ አጠቃቀም ሥርዓተ ጽሕፈትን በመጠቀም ሕዝብን ሊያስተምሩ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ፡፡

Source link

The post በቲቢ በሽታ የመያዝ መጠንን በ90 በመቶና የመሞት መጠንን በ95 በመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ first appeared on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. mesfin

    ውሸት የማይሰለቸው የባንዳ ስብስብ !! ሆዳሞች

Leave a Reply