በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር በግብጽ ምክንያት ስምምነት ላይ አለመደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ የ…

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር በግብጽ ምክንያት ስምምነት ላይ አለመደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

አምባሳደር ዲና እንዳሉት ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን ከትናንት በስቲያ በበይነ መረብ በመታገዝ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በቀጣይ ፍሬያማ ውይይት እንዲካሄድ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎችን ባካተተ መንገድ ውይይት ይደረግ የሚል ሃሳብ አቅርባለች።

ሱዳን በኢትዮጵያ ሀሳብ የተስማማች ቢሆንም ግብጽ ግን ሀሳቡን ውድቅ እንዳደረገች አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ ኢትዮጵያ ይሄንን ሀሳብ ያቀረበችው ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል ነው።

አምባሳደር ዲና በሌሎች ጉዳዮችም መግለጫ የሰጡ ሲሆን ከአረብ ኢሚሬት በኢንቨስትመንት በቴክኖሎጂ አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከህንድ ደግሞ 5 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የኮቪድ መከላከያ የሚውል ድጋፍ ማግኘቷን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ 580 የህንድ ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን በኬሚካል ምርት፣ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፣ኮንስትራክሽን እና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይም ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ሌሎች የጎረቤት አገራት የኢትዮጵያ ሰላም የእነሱም ሰላም እንደሆነ ማረጋገጣቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply