በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ…

በታላቁ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በደብረ ሊባኖስ ገዳም በጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል ውስጥ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ መሆኑ ታውቋል። ታህሳስ 30/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በገዳሙ የጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል በተነሳው የእሳት አደጋ ከ20 በላይ ክፍሎችም የወደሙ መሆኑ ተገልጧል። እሳቱ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከትል በገዳሙ መነኮሳት፣ በአካባቢው ምእመናን እና በጸጥታ ኃይል አባላት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ተገልጿል ሲል የማህበረ ቅዱሳን አገልግሎት ያጋራው መረጃ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply