በታሪክ ከማልዘናጋቸው ነገሮች አንዱ የአማራው ልዩ ሃይል ተግባር ነው! “መቶ አለቃ ሺብሩ ጌትነት” ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) እውነት ነው “የአማራ ልዩ ሃይል” ተዋጊ ነው።…..

በታሪክ ከማልዘናጋቸው ነገሮች አንዱ የአማራው ልዩ ሃይል ተግባር ነው! “መቶ አለቃ ሺብሩ ጌትነት” ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) እውነት ነው “የአማራ ልዩ ሃይል” ተዋጊ ነው።… የአርቢት፣የደብረዘቢጥ እና የጋሺና ምሺጎችም ይመሰክራሉ። ልዮ ሃይሉ ከብዙ ተቋሞች የተወጣጣ የአማራ ህዝብ መከታ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን ነው። እውነት ነው የአማራ ህዝብ የምንጊዜም ጠበቃ ነው። ጠላትን በየአቅጣጫው እየደመሰሰ የማይዝል ክንዱን እየቀመሰ ይገኛል። የአማራ ልዩ ሃይል ተጠናክሮ መቋቋም ከጀመረበት 2011 ዓም ጀምሮ ያለ ዕረፍት እየተዋጋ ያለ ሃይል ነው። በዚህም በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ያለ ዕረፍት የተዋጋ ሰራዊት ነው። ሰራዊቱ ከቅማንት ፀንፈኛ ቡድን፣ከትህነግ፣ ከኦነግ ሸኔ፣ከቤሻንጉል አማፂ ጋር ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ተዋግቶ ጠላቶቹን አሳፍሯል። በሁሉም የአማራ ምድር ላይ ደሙን አፍስሷል አጥንቱንም ከስክሷል። ስለሆነም ወድ ወገኔ ሆይ ከአማራ ልዩ ሃይል ጎን ልንቆም ይገባል። እውነት ለመናገር በትንሺ ክፍያ ውድ ህይወቱን እያጣ ያለውን ልዩ ሃይላችንን አይዟችሁ ልንላቸው ይገባል። የአማራ ልዩ ሃይል ጀግና ሰራዊት መሆኑንም እንድህ ያሉ መስመራዊ መኮነኖችም እየመሰከሩለት ነው። ስለዚህ እየተከፈለልን ላለው ነገር ሁላችንም ልናመሰግነውና ልናበረታታው ያስፈልጋል። ክብርም ልንሰጣቸው ይገባል። የአማራው የመንግስት አስተዳደሮችም ልዩ ሃይላችንን የመንከባከብ ግደታ አለባችሁ። ስለሆነም ክብር ለልዩ ሃይላችን እንላለን። © አሸናፊ ገናን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply