በታንዛኒያ 155 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በምስራቅ አፍሪካ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በታንዛንያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ህይወት ማለፋ ተነግሯል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስታወቀው በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የ155 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 2 መቶ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል።

በሁለት ሳምንት ውስጥ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የሞቾቹ ቁጥር በተለይም በከተማዋ ዳሬሳላም እና በባህር ዳርቻ በእጥፍ መጨመሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማጃሊዋ ለፖርላማ እንደተናገሩት፤ የኤልኒኖ
የአየር ትንበያ ሁኔት የአየር ንብረቱ ለሳምንታት የጣለውን ከባድ ዝናብ አባብሶታል ሲሉ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች በተከሰተው ጎርፍ ምክንያት ተዘግተው በአደጋ ጊዜ ለተጎዱ መቆያ ሆነዋል ተብሏል።

ከ51 ሺህ በላይ አባወራዎች በዝናቡ መጎዳታቸውን የተገለፀ ሲሆን፤ በቆላማ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች ወደ ከፍተኛ ስፍራዎች ላይ እንዲሄድ ሚንስትሩ አስጠንቅቀዋል ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply