በታጣቂዎች ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸው ለተፈናቀሉ አማራዎች ድጋፍ ተደረገ የአማራ ሚዲያ ማእከል ጥቅምት 15 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በጉራፈርዳ ሸኮ እና አሮጌብርሀን ቀበሌ ጥቅ…

በታጣቂዎች ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸው ለተፈናቀሉ አማራዎች ድጋፍ ተደረገ የአማራ ሚዲያ ማእከል ጥቅምት 15 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በጉራፈርዳ ሸኮ እና አሮጌብርሀን ቀበሌ ጥቅምት 8 ለ9 እና ጥቅምት 11ለ12 አጥቢያ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸው ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ አማራዎች የ100 ኩንታል እህል ድጋፍ ተደረገ። ጭፍጨፋውን የሰሙ እና ወገኖቻችን ምን ደረሰባቸው ብለው ሚዛን ድረስ ሂደው ድጋፍ ያደረጉት አማራዎች ለዝግጅት ክፍላችን ማዘናቸውን እና ያሉበት ጉዳት ከባድ መሆኑን ገልጸውልናል። በተጨማሪም የደቡብ ክልል ልዩ ሀይሎች እርዳታውን ሊያደርሱ በሄዱበት ወቅት ከፍተኛ እንግልት የፈጸሙባቸው ሲሆን የመጣችሁት ፎቶ አንስታችሁ ለመሄድ ነው በሚል የሞባይል ስልካቸውን ተቀምተው እንደነበር ለማወቅ ችለናል። ድጋፍ ሊያደርግ የሄደው የአማራዎች ስብስብም ” ወገኖቻችን ሲታረዱ ሳታድኗቸው ፎቶ ወጣ አትበሉ። የወገናችንን የመጨረሻ ማስታወሻ ማስቀረት አለብን “በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ስልካቸውን መቀበላቸውን ነግረውናል። አያይዘውም የደቡብ ክልል ልዩ ሀይሎች በተፈናቃይ የአማራ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እንደሚያደርሱባቸው እና እንደሚያንገላቷቸው የገለጹልን ሲሆን የተፈናቃዮች ፍላጎትም ልዩሀይል ከአካባቢው እንዲወጣ እና ወደቦታቸው ተመልሰው የመኖር ዋስትና ተሰጧቸው ኑሯቸውን መቀጠል እንደሚፈልጉ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply