በቴነሲ አውሎ ነፋስ ስድስት ሰዎችን ገደለ

https://gdb.voanews.com/8545af99-f4d9-41ca-8372-420dc89bce79_w800_h450.jpg

በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት በደረሰው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ይገኛሉ።

የአደጋ ሠራተኞች ፍርስራሹን በማጽዳት ላይ ሲሆኑ፣ የግዛቲቱ መንግስት ባለሥልጣናት የስድስቱ ሰዎችን መሞት  እንዳረጋገጡ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ትናንት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በመጣው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ፤ መኪኖች፣ ቤቶች እና ሕንጻዎች የወደሙ ሲሆን፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠባቸው ታውቋል።

የመብራት እና የአደጋ ሠራተኞች ሥራቸውን ማከናወን እንዲችሉ፣ አደጋው በደረሰባቸው አውራጃዎች የሰዓት እላፊ ታውጆ፣ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተደርጓል።  

Source: Link to the Post

Leave a Reply