በትህነግ ህገወጥና ዘራፊ ቡድን በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን…

በትህነግ ህገወጥና ዘራፊ ቡድን በኃይል ተገደው ወደ ጦርነት የገቡ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በሰላማዊ መንገድ እየገቡ ነው፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የልዩ ኃይል አባላቱ በዳንሻ ለተገኘው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ጋር መዋጋታችን ትክክል አልነበረም ብለዋል፡፡ ይህንን በማመንም በሰላማዊ መንገድ ወደ አማራ ክልል ገብተናል ነው ያሉት፡፡ “እኛ የቆምንለት ዓላማ ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንጂ ለትህነግ ህገወጥ ቡድን አይደለም“ ያሉት የልዩ ሃይል አባላቱ ወደ አማራ ክልል ከገቡ በኃላም በእንክብካቤ እንደተያዙ ተናግረዋል፡፡ “የትግራይ ህዝብ በህገወጡ የትህነግ ቡድን ከሚደርስበት በደል ለመውጣት ከሃገር መከላከያ ሰራዊት እና ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር እንዲሰለፍም እንጠይቃለን“ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ የትግራይ የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል በመግባት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ሲል አብመድ ዘግቧል። በርካታ ህወሀት ያስገደዳቸው የልዩ ሀይል አባላት ለአሸባሪ ቡድን ስልጣን ሲባል ከወገን ጋር ጦርነት አልገጥምም በማለት በተለያዩ አካባቢዎች ለተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊት በሰላም እጃቸውን እየሰጡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply