በትሕነግ አገልጋዮች በግፍ የተገደሉት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት የዘውዱ ገ/እግዚአብሔር እና ሙላው ከበደ የአጎበር(የለቅሶ) ስነ ስርዓት በቃፍታ ሁመራ ተካሄደ።…

በትሕነግ አገልጋዮች በግፍ የተገደሉት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት የዘውዱ ገ/እግዚአብሔር እና ሙላው ከበደ የአጎበር(የለቅሶ) ስነ ስርዓት በቃፍታ ሁመራ ተካሄደ።…

በትሕነግ አገልጋዮች በግፍ የተገደሉት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት የዘውዱ ገ/እግዚአብሔር እና ሙላው ከበደ የአጎበር(የለቅሶ) ስነ ስርዓት በቃፍታ ሁመራ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትሕነግ አገልጋዮች ታህሳስ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ደለሎ የእርሻ ልማት ላይ በግፍ በጥይት የተገደሉት ዘውዱ ገ/እግዚአብሔር እና ሙላው ከበደ በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባል በመሆን ሲታገሉ ነበር። ከምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮርሁመር/ጠረፍ ወርቅ ቀበሌ ወደ መተማ ደለሎ ወጣቶችን ለመግደል ያቀናው የትሕነግ አገልጋይ ጦር ሁለቱን አፍኖ በጥይት ቢገድልም ዘውዱገ/እግዚአብሄር ከመመታቱ በፊት በሰጠው የአፀፋ ምላሽ 4 የአገዛዙ ወታደሮችን መግደሉ ይነገራል። አቶ ይልማ ፈረደ የተባለሉ የወልቃይት ጠገዴ ባለሃብትም “ሽፍቶችን” አስጠግተሃል በሚል ታስረው ወደ መተማ ሲወሰዱ የአገዛዙ የበላይ አመራሮች “እዚህ ድረስ ለምን አመጣችሁት? እዛው በጥይት አብራችሁ አትጨርሱትም ነበር” በሚል ወታደሮችን ሲያዋክቡ እንደነበርም መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱም የእነ ዘውዱ ገ/እግዚአብሄር እና ሙላው ከበደ ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶች ተሰባስበው ሀዘናቸውን በቅጡ እንዳይገልፁ ተከልክለው እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ በተከፈለው ከባድ መስዋዕትነት ነጻ በወጣ ማግስት ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የማንነት ታጋዮቹን እነ ዘውዱ ገ/እግዚአብሄርንና ሙላው ከበደን በቃፍታ ሁመራ ሽሃሽም ቀበሌ የአጎበር (የለቅሶ) ስነ ስርዓት በማዘጋጀት በድምቀትና በነጻነት ዘክሮ መዋሉን የነገረችን የአካባቢው ወጣት ራሄል ማለደ ትባላለች። “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አባል ነሽ፣ኮሚቴዎች ከቤትሽ እንዲሰበሰቡ አድርገሻል፣ጎንደር ሄደሽ ከኮሚቴው አመራሮች ጋር መክረሻል፣የአምሳልን፣የፋሲልንና የመሀሪን ሙዚቃ በሆቴልሽ ከፍተሻል” በሚል በተደጋጋሚ በቃፍታ እስር ቤት ስትታሰርና ስትፈታ የነበረች ታጋይ ነች። ራሄል ማለደ በትሕነግ አገዛዝ ስለደረሰባት ግፍ እና በደል እንዲሁም ስለተሰውት እና ዛሬ የአጎበር ስነ ስርዓት ስለተደረገላቸው ዘውዱ ገ/እግዚአብሄር እና ሙላው ከበደ ሲያደርጉት ስለነበረው የትግል እንቅስቃሴ እና ስለከፈሉት መስዋዕትነት ከአሚማ ጋር ቆይታ አድርጋለች። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply