በትረምፕ ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ጠበቆቻቸው የይግባኝ ፍ/ቤትን ጠየቁ

https://gdb.voanews.com/01000000-c0a8-0242-d13c-08dbe7d80f04_w800_h450.jpg

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በእ.አ.አ 2020 የተደረገውን ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ሞክረዋል በሚል የተመሠረተባቸውን ክስ አስመልክቶ፣ ስለጉዳዩ  ከፍርድ ቤት ውጪ እንዳይናገሩ ጉዳዩን በሚመለከቱት ዳኛ የተጣለባቸው እገዳ እንዲነሳ፣ ጠበቆቻቸው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ጠይቀዋል።

የትረምፕ ጠበቆች ዛሬ በፍርድ ቤት እንደተናገሩት፣ እገዳው የፖለቲካ ንግግርን የሚገታ ውሳኔ ነው ብለዋል።

የልዩ ዓቃቤ ሕግ ጠበቆች በበኩላቸው፣ ትረምፕ ክሱን በተመለከተ ከሳሽ ጠበቆችን እና ምስክሮችን በተመለከተ ከፍርድ ቤት ውጪ የሚናገሩት የሚያጥላላ ንግግርን ለማስቆም እገዳው አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ትረምፕ ከፍርድ ቤት ውጪ የሚሰጡት አስተያየት፣ የፍትህ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዳይኖር የሚያደርግ እና ምሥክሮችን የሚያስፈራራ ነው ሲሉ ከሳሾች ይከራከራሉ። የትረምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፣ እገዳው የትረምፕን የመናገር ነፃነት የሚገድብ እና ኢ-ሕገመንግስታዊ ሲሉ ይከራከራሉ።

የይግባኝ ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ውሳኔ እንደማይሰጥ ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply