በትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተረጋገጠ

በትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆኑ በሴኔቱ ፀደቃላቸው።
 
የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ሳምንት በቀረበት ወቅት ኤሚ ኮኒ ባሬት ከ9ኞቹ አንዷ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው መመረጣቸው ለዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ድል ነው ተብሏል።
 
ሪፐብሊካኖቹ 52 ለ48 በሆነ የድምፅ ብልጫ ከምርጫው በፊት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት እንዳይፈፀም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያደርጉ የቆየቱትን ዲሞክራቶች በማሸነፍ ነው ሹመቱ እንዲፀድቅ አድርገዋል።
 
የ48 ዓመቷ የከፍተኛ ፍርድ ዳኛ በመሆን የተሾሙት ኤሚ ኮኒ ባሬት ትናትሽ ምሽት ከዶናልድ ትራምፕ ጎን ሆነው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
 
ይህ ኤሚ ኮኒ ባሬት ሹመት በቀጣይ ዘመናት ወግ አጥባቂዎቹ በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ 6 ለ 3 ብልጫ እንዲኖራቸው በማድረግ የሚፈልጉት ውሳኔ በቀላሉ እንዲያሳልፉ ያስችላቸዋል የሚል ግምት እንዲቀመጥ አድርጓል።
 
በሜይን ድጋሜ ለመመረጥ ከፍተኛ ትግል የሚጠብቃቸው ሴናተር ሱሳን ኮሊን የትራምፕ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት የተቃወሙ ብቸኛዋ ሪፐብሊካን ናቸው።
 
ይህ የዶናልድ ትራምፕ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በፈረንጆቹ 2017 ኔኢል ጎርሰችን እና በ2018 ብሬት ካቭኖ ቀጥሎ ሶስተኛዋ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

The post በትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተረጋገጠ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply