በትናንቱ የ10ሺዎች ተቃውሞ ሰልፈኞች የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች አራቱን ገደሉ

የሱዱን ጸጥታ ኃይሎች በትናንትናው እለት ካርቱም ውስጥ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ተካፋይ የነበሩ 4 ሰዎችን መግደላቸውን የአገሪቱ የህክምና ባለሙያዎች ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞ ተካፋይ የሆኑበት የትናንቱ የተቃውሞ ሰልፍ ለ11ኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑን ተገልጿል፡፡ 

የዲሞክራሲ ደጋፊ የሆኑት ተቃዋሚዎች ላለፉት ሁለት ወራት ያለማቋረጥ በተካሄደው ተቃውሞ እስካሁን 52 ሰዎች መገደላቸውን የነጻነት ትግሉ ተሳታፊ የሆነው የሱዳን ሀኪሞች ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

የትናንቱን ተቃውሞ ተክትሎ በካርቱም የኢንተርኔትና የሞባይል ስልክ አገልግሎት የተቋረጠ መሆኑን ሲዘገብ ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ የስልክ መስመሮች መከፈታቸው ተነግሯል፡፡

በካርቱም የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ግድያውንና ኃይል መጠቀምን ያወገዘ ሲሆን “የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች በሚዲያ ተቅቋማትና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ” አሳስቧል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በተወካዩ አማካይነት ለጥሰቱ ተጠያቂ በሆኑት ላይ ትክክለኛው ማጣራት እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

ሰልፈኞቹ የተደቀንባቸው የደህንነት አደጋ ሳያግዳቸው “ወታደራዊ አገዛዝን አንፈልግም!” የሚለው መፈክራቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply