በትናንትናው እለት ከ8 መቶ በላይ ሰነድ አልባ ፍልሰተኞች ከሳውዲ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፍልሰተኞች አስመላሽ ብሄራ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/p0qjdCts0Wn0xOBh9HI_43Epy2a8kaDWy2wkb856fR3teYTpwEbttuZDjBeUgtH4BKJtESNYrlRhwGXCq6xgjKjStbhbWQ4UQtCmPYIG6DPdsjI8RTxh0s0UoUeSovDFyrCQTHhGl6DUHUnUz9wMsTIgoMFxWP09FV-k7wyCUkV0wNoIPvSK3knfbK2T5azIIwDNhXdAB5FmUHxn9fL4ef1xTfVCOZ87ccY4NR1MKRwBcX194npt4UpVnLU57c8r792IjcYSMaBP3lKVXsjRVR5qhfXTapjPdyM2Hga3bRlN7wrFo5_617s8118w3cXDui327Q3oqSHptyJsW8rnCA.jpg

በትናንትናው እለት ከ8 መቶ በላይ ሰነድ አልባ ፍልሰተኞች ከሳውዲ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የፍልሰተኞች አስመላሽ ብሄራዊ ኮሚቴ በትናንትናው እለት ከሳዑዲ ዓረቢያ በኹለት በረራዎች 842 “ሰነድ አልባ” ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መልሷል፡፡

ፍልሰተኞቹ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማጎሪያ ቦታዎች የቆዩ መሆናቸውንም ሚንስቴሩ ገልጧል።

በቀጣዮቹ አራት ወራት ፍልሰተኞቹን ለማጓጓዝ በሳምንት 12 በረራዎች በተከታታይ ይደረጋሉ የተባለ ሲሆን ትናንት 842 ፍልሰተኞች ወደ ሃገራቸው ገብተዋል፡፡
ትናንት በተጀመረው ሦስተኛው ዙር ፍልሰተኞችን የመመለስ መርሃ ግብር 70 ሺህ ዜጎች ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቀደም ሲል መገለጹ አይዘነጋም፡፡

ቀደም ሲል በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለይም በሳውዲ አረቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ሚገኙ ወገኖችን መንግስት እንዲደርስላቸው ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል በመንግስት ላይ ግፊት ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply