በትግራዩ ጦርነት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ትናንት ከተባበሩ መ…

በትግራዩ ጦርነት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ትናንት ከተባበሩ መንግስት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮምሽን ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ መንግስት የተቀረፀው የሽግግር ፍትሕ ፓሊሲ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ ገልጸዋል።

በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙት ወንጀሎች በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እየሠራሁ ነው የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ በኩል ተቃውሞ ደርሶበታል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ከወራት በፊት ለኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በፃፉት ደብዳቤ የሽግግር ፍትሕ ፓሊሲውን መተቸታቸው ይታወሳል ። 

በፌደራሉ መንግስት የተቀረፀው የሽግግር ፍትሕ ፓሊሲ የፕሪቶርያውን ስምምነት መሰረት ያላደረገ፣ የትግራይን ልዩ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ የትግራይን ወሳኝ ተሳትፎም ያላካተተ ሲልም መግለጻቸው ይታወሳል ።

አቶ ጌታቸው ረዳ፦ «…የሽግግር ፍትሕ ተጠያቂነት ያረጋግጣል ብለን የምናስብ ከሆነ፥ በኤርትራ የተፈፀሙትስ ብለን ማንሳት ይጠበቃል።

ባሉት መረጃዎቻችን መሰረት 75 በመቶ የሚሆን የፆታ ጥቃት የፈፀሙ የኤርትራ ሐይሎች ላይ እንዴት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይቻላል ?»  ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፌዴራሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም ።

መጋቢት 11ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply