በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት እርዳታ የሚፈልገው የህዝብ ቁጥር 4.5 ሚሊየን እንደደረሰ  የትግራይ ክልል ሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ሀላፊ አቶ  አብርሃ ደስታ አረጋግጠዋል፡፡  ( አሻራ ታህሳ…

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት እርዳታ የሚፈልገው የህዝብ ቁጥር 4.5 ሚሊየን እንደደረሰ የትግራይ ክልል ሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃ ደስታ አረጋግጠዋል፡፡ ( አሻራ ታህሳ…

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት እርዳታ የሚፈልገው የህዝብ ቁጥር 4.5 ሚሊየን እንደደረሰ የትግራይ ክልል ሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃ ደስታ አረጋግጠዋል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 27፣ 2013ዓ.ም) በትግራይ ከ4 ሚሊየን ሰዎች ልዮ ልዮ እርዳታ የሚሹ ሲሆን፣ በመቀሌ ብቻ ከ300 ሺ በላይ እርዳታ ይፈልጋል ብለዋል- አቶ አብርሃ ደስታ፡፡ አቶ አብርሃ የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን አሁን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር አባል ሆነው ብልፅግናን ተቀላቅለዋል፡፡ በሌላ በኩል የመቀሌ ከንቲባ አቶ አታክልቲ የመቀሌን ነዋሪ ያወያዮ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች ለምን ወደ ትግራይ ገቡ የሚል ጥያቄ ከማህበረሰቡ ተነስቶ ከንቲባው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች የገቡት የሰሜን እዝን ህወኃት ስላወደመው ኢትዮጵያን ለማዳን ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች እንደተሳተፉም ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት የመጀመሪያው ፍንጭ ሰጭ ባለስልጣን ሲሆኑ፣ እነ አሜሪካ ቀድመው የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት እንደተሳተፉ ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠው ነበር፡፡ በሌላ በኩል በውቅሮ የአልነጃሽ መስጊድ እና የአማኑኤል ቤተክርስቲያን ጉዳት የደረሰባቸው በአካባቢው ምሽግ ስለነበር እንደሆን የአልነጃሽ ኢማም እና አስጎብኝ ገልፀዋል፡፡ በየአብያተእምነቶች ምሽግ አይሰራ ብንልም ሰሚ አጥተን ነበር፡፡ የፈራነው ደረሰ ሲሉ የኢቴቪ ተናግረዋል፡፡ ውጊያውም ከየአብያተእምነቶች አጠገብ እንደነበር የሀይማኖት አባቶች ተናግረዋል፡፡ አሻራ ቀደም ሲል ህወኃት በየቤተእምነቶች ምሽግ ቆፍሮ ትጥቁን ማከማቻ እንዳደረገ ዘግበን ነበር፡፡ የህወኃት አመራሮች ድል ከተነሱ በኃላም ሸህ እና ቄስ መስለው በየአብያተ እምነቱ እንደሚገኙ እና እንደተገኙ ከሁለት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት ይፋ አድርጓል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply