በትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ መገደሉ ተገለጸ

https://gdb.voanews.com/4317DF2F-41DD-4A4B-A44B-D00772627E30_cx0_cy5_cw0_w800_h450.jpg

በትግራይ ቴሌቪዥን የአማርኛ ክፍል ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ በጥይት መገደሉ ተገለጸ። ጋዜጠኛው ትናንት ማታ ከአንድ አንድ ጓደኛው ጋር መኪና ውስጥ እንዳለ የተገደለውም በመንግሥት የፀጥታ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ነው ሲሉ ጓደኞቹ እና የሥራ ባልደረቦቹ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ አለማሳካቱን አክሎ የቪኦኤ ዘጋቢ ከስፍራው ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply