በትግራይ እየተካሂያደ ላለዉ የጦርነት ተፈናቃዮች/ተጎጅዎች እርዳታ ሊያሰባስቡ የተነሱ አርቲስቶችን ማበረታታት እንጂ መዉቀስ አይገባም:: ———————– ይልቅስ በዳተ…

በትግራይ እየተካሂያደ ላለዉ የጦርነት ተፈናቃዮች/ተጎጅዎች እርዳታ ሊያሰባስቡ የተነሱ አርቲስቶችን ማበረታታት እንጂ መዉቀስ አይገባም:: ———————– ይልቅስ በዳተኝነት ለጥ ብሎ የተኛዉን እጅግ ብዙዉን አርቲስት በመላ ሀገሪቱ ተፈናቅሎ:ተገሎ እና የዘር ፍጅት እየተደረገበት ያለዉን የአማራ ህዝብ እንዲሁም የተዋህዶ እምነት ተከታዩን ህዝብ እንዲያግዝ/እንዲረዳ ጨቅጭቁት: ቀስቅሱት ተቹት ብሎም አበረታቱት ! ——————– ሸንቁጥ አየለ… ————- ጥቅል ሀሳብ ———– በትግራይ እየተካሂያደ ላለዉ የጦርነት ተፈናቃዮች/ተጎጅዎች እርዳታ ሊያሰባስቡ አርቲስቶችን ማበረታታት እንጂ መዉቀስ አይገባም::ይልቅስ በስፋት በዳተኝነት በአያገባኝም ባይነት: በማይረባ ይሉኝታ እና በከንቱ ፍርሃት ለጥ ብሎ የተኛዉን እጅግ ብዙዉን አርቲስት በመላ ሀገሪቱ ተፈናቅሎ:ተገሎ እና የዘር ፍጅት እየተደረገበት ያለዉን የአማራ ህዝብ እንዲሁም የተዋህዶ እምነት ተከታዩን ህዝብ እንዲያግዝ/እንዲረዳ ጨቅጭቁት: ቀስቅሱት ተችሁት ብሎም አበረታቱት:: ኢትዮጵያዊ ቅድስናችሁን አትርሱ::የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም እግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ያለዉ ህዝብ መሆኑን አትርሱ::የኢትዮጵያን ቅድስና በጎሳ ፖለቲካ ካንሰራማ አስተሳሰብ ያቆሸሹትን ሁሉ እግዚአብሄር ከስራቸዉ ነቅሎ እንዲያጠፋቸዉም ጸልዩ:: ——————– -በዚህ ጦርነት እየተጎዳ ያሉት ሴቶች እና ህጻናት እንዲሁም አቅመ ደካማዎች ናቸዉ::የኢትዮጵያን ህዝብ ዘረኝነት ወስጥ ወስዶ የመሰገዉ የህዉሃት:የሻቢያ: የኦነግ/የኦህዴድ:የብአዴን: የደህዴን አሁን ደግሞ የብልጽግና የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ:: በዚህ ፍልስፍና የአማራ ህዝብ ለሰላሳ አመታት ተቀጥቅጦበታል::እጅግ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ተፈጽሞበታል:: -በዚህ ፍልስፍና ፕሮፌሰር አስራት ቀድመዉ እንዳስጠነቀቁት ገና የትግራይ ህዝብ አገር አልባ ይሆንበታ:: -በዚህ ፍልስፍና የተነሳ ለሃያ አመታት ሙሉ ደጋግመን ለኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን እንዲሁም አሁን ለሚመሩት የብልጽግና የኦሮሞ አክራሪ የፖለቲካ መሪዎች እንዳሳሰብነዉ የኦሮሞ ህዝብ ሀገር አልባ ይሆንበታል:: -በዚህ ፍልስፍና ለመላዉ ኢትዮጵያዊ ለ87 ሰባቱም ነገዶች ደጋግመን እንዳስጠነቀቅነዉ ሁሉም ነገድ ሀገር አልባ ይሆንበታል:: ሆኖም በርካታዉ ሰዉ በተለይም ሀሳባቸዉ በጎሳ ፖለቲካ ካንሰርማ አስተሳሰብ የተመታዉ የዚህ ዘመን ልሂቃን የጎሳ ፖለቲካ እዳ በአማራ ህዝብ የዘር ፍጅት ላይ የሚያበቃ ስለመሰላቸዉ ነገሩን በፈገግታ ሲከታተሉት ነበር:: -የትግራይ ህዝብ እግዚአብሄር ህዝቤ ያለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ነዉ::የሰይጣን መንፈስ የተጠናወታቸዉ ህዉሃታዉያን እንደሚሉት የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ያለዉ የትግራይም ህዝብ የተለዬ ህዝብ አይደለም::ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተቀደሰ ህዝብ ነዉ::ይሄን ቅድስና የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሀይሎች አርክሰዉታል::በዚህም መላዉ ኢትዮጵያ እንድትረክስ አድርገዋታል:: እናም የኢትዮጵያዉያን ደም በብዙ ምክንያትም እየፈሰሰ ይቀጥላል:: -አሁን በሁለቱ ዘረኛ ፓርቲዎች ማለትም በህዉሃት እና በኦህዴድ/ብልጽግና መሃከል በተነሳ የስልጣን ትግል ህጻናት እና ሴቶች በትግራይ ሰለባ እየሆኑ ነዉ::የእነዚህ ህጻናት እና ሴቶች እንዲሁም አቅመ ደካሞች ወገኖቻችን መጎዳት ያገባናል ያሉ አርቲስቶች ተነስተዉ ለመርዳት የመሰላቸዉን እርምጃ ቢወስዱ ነገሩ የሚበረታታ ነዉ:: በዚህ የሁለት ዘረኛ ሀይሎች (አቢይ መራሹ እና ደብረጺዮን መራሹ የርኩስ መንፈስ ተሸካሚ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ ሀይል) ጦርነት ምክንያት ለሚጎዱ የትግራት ህጻናትን:ሴቶችን እና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት ጎፈንድ ከተከፈተ እኔም የአቅሜን አግዛለሁ:: የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነዉ::የትግራይ ህዝብ የተቀደሰዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ነዉ::የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ የነጠለዉ:የኢትዮጵያን ህዝብ እርስ በርሱ የነጣጠለዉ ህዉሃት እንዲሁም የሻቢያ: የኦነግ/የኦህዴድ:የብአዴን: የደህዴን አሁን ደግሞ የብልጽግና የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍና ነዉ:: ስለሆነም ለትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች ገንዘብ ሰብስበዉ ለመርዳት የተነሱ አርቲስቶችን አታሸማቋቸዉ::አበረታቷቸዉ እንጅ::ይልቅስ በስፋት የተኛዉን እጅግ ብዙዉን አርቲስት በመላ ሀገሪቱ ተፈናቅሎ:ተገሎ እና የዘር ፍጅት እየተደረገበት ያለዉን የአማራ ህዝብ እንዲሁም የተዋህዶ እምነት ተከታዩን ህዝብ እንዲያግዙ ጨቅጭቋቸዉ::ቀስቅሷቸው::ተቿቸዉም:: በተለይም ክርስቲያን ኦርቶዶክስ የሆኑት አርቲስቶች በጀዋራዉያን/ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ወንጀለኛ የዘር ማጥፋት ተከናዉኖበት ክርስቲያኑ ህዝባችን መጠለያ አጥቶ ሲያልቅ ዝም ማለታቸዉ ነዉር እንደሆነ ስም እየጠቀሳችሁ ጻፉባቸዉ::ተነሱ ህዝባችሁን አግዙ እያላችሁ ጨቅጭቋቸዉ::በዉስጥም በዉጭም እረፍት ንሷቸዉ:: በተለይም በነገድ ከአማራ የተገኙ አርቲስቶች የአማራ ህዝብ እንዲህ ከዉሻ ባነሰ ሁኔታ ከመላ ሀገሪቱ ተፈናቅሎ መጠጊያ ሲያጣ ሊረዱት ሲችሉ አንረዳህም ወገንህ አይደለንም ብለዉ እንቢ በማለታቸዉ ዉቀሷቸዉ::ጨቅጭቋቸዉም::ተቿቸዉም:: አንዳንዴም በስልት አበረታቷቸዉ:: ሌላዉ ማስታወስ ያለባችሁ እንትና የተባለች/የተባለ አርቲስት የዘር ፍጅቱን ተቃወመች/ተቃወመ ብላችሁ እሷን/እሱን በማወደስ ብቻ የምታቆሙት ነገር በቂ እንዳልሆነ ነዉ::ማድረግ ያለባችሁ የዘር ፍጅቱን እና ማፈናቀሉን ማዉገዝሽ/ማዉገዝህ ጎበዝ ያስብልሻል/ያስብልሃል::ሆኖም እየተገደለ ያለዉን ህዝብ:እየተፈናቀለ ያለዉን ህዝብ እና የዘር ፍጅት እየተደረገበት ያለዉን የአማራ ህዝብ እንዲሁም የተዋህዶ እምነት ተከታዩን ህዝብ እንዲሁም የጥቃት ሰለባ የሆኑ ልዩ ልዩ ነገዶችን የማገዝ ግዴታ አለባችሁ እያላችሁ ማጀገን ነዉ::የማጀገን ሂደቱ ከተቃዉሞ እስከ የድርጊት እንቅስቃሴ እንዲሄድ ጫና ማድረግ ነዉ::አዎንታዊም አሉታዊም ጫና ሊሆን ይችላል:: ጥያቄዉ ግን አርቲስቶቻችን ይሄን ያህል ልበ ጨካኝ የሆኑት ምን ሆነዉ ነዉ?በተለይ አማራ የሆኑት አርቲስቶች የአማራ ህዝብ ይሄን ያህል የዘር ፍጅት ሲደረግበት ለምንድን ነዉ ቱፍም ቡፍም ለማለት እንቢ ያሉት?ነዉ ወይስ ነገሩ እነሱ ጋ የማይመጣ መስሏቸዉ ነዉ?ይሄን ሁኔታ እያብራሩ እና ነገ የዘር ፍጅቱ ወደ ራሳቸዉ ቤት እንደሚመጣ እያብራራችሁ አስረዷቸዉ::ህዉሃት ለጊዜዉ ቢደክም የጎሳ ፖለቲካ ቫይረስ በኢትዮጵያ ምድር ጉልበቱን እያጠነከረ እንደመጣም አብራሩላቸዉ::አርቲስት ጎበዝ ተማሪ መሆኑን አትርሱ::ቢሆንም ጎበዝ አስተማሪም ይፈልጋሉ:: ለማስሌ የአማራ አርቲስቶች አስተማሪ እንደሚፈልጉ የሚከተለዉን ሀቅ ተመልከቱት:: የአማራ አርቲስቶች በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለዉን ህዝብን ፍጅት ማዉገዝን እንደ ዘረኝነት በመቁጠር ገዳይ ኦነጋዉያንን እና ተገዳይ አማራን አትግደሉ ብሎ ለሰላሳ አመታት የሚታገለዉን ሀይል እኩል ሚዛን አስቀምጠዉ ሲሳለቁ የሚዉሉ ናቸዉ::ለዚህ ማሳያዉም ኢቢኤስ ላይ የተለያዬ ፕሮግራም ላይ የሚሰሩ የአማራ አርቲስቶችን ማስተዋል በቂ ነዉ::ነገራቸዉ ሁሉ የለበጣ ነዉ::የዘር ፍጅት የሚደረግበትን የአማራ ህዝብ ከኦነጋዊ/ቄሮአዊ/ኦህዴዳዊ ሀይል ጋር እንደ አቢይ አህመድ መግለጫ በአንድ አረፍተ ነገር ሁሉንም በመኮነን/በመምከር የሚያልፍ ነዉ:: ይሄ ታላቅ ለበጣ ነዉ::ይሄ ታላቅ ጭካኔ ነዉ::ገዳይን ለይቶ እና በስም ጠርቶ ማዉገዝ ሲገባ : ተገዳይ/ተፈናቃይን ደግሞ በስም ጠርቶ ማገዝ መደገፍ ብሎም ፍትህን ቁልጭ አድርጎ መናገር ሲገባ የአማራ አርቲስቶች ነገር ግን ታላቅ ለበጣ እና ስላቅ ነዉ::በጣም የሚያሳዝነዉ ነገ የነሱንም አንገት ሊቀላ ኦነጋዊ/ኦህዴዳዊ/ቄሮአዊ/ጀዋራዊ ሀይል ወደነሱ እንደሚመጣ መካዳቸዉ ጭምር ነዉ::የህዉሃትን የዘር ፍጅት ሀያ ሰባት አመታት የካዱት እነዚህ አርቲስቶች አሁንም ያንኑ ክህደታቸዉን ቀጥለዋል::እዚህ ላይ በተለይ የአማራ አርቲስቶች ላይ ያተኮርኩበት ዋና ምክንያት ሀላፊነቱን:ቀዳሚነቱን አስተባባሪነቱን መዉሰድ ያለባቸዉ እንዲሁም የቀሪ ኢትዮጵያዊ አርቶስቶችን ማስተባበር ያለባቸዉ እነዚህ ከነገደ አማራ የተገኙ የአማራ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ዘራፍ ብለዉ መነሳት ያለባቸዉ ሰዎች መሆናቸዉን ለማጠዬቅ ነዉ:: አንድ ሰዉ እራሱ ጮሆ ድረሱልኝ ሳይል ሌሎች ተጎድተሃል ብለዉ ሊደርሱለት አይችሉም እና የአማራ ሰዉ ሁሉ ስለ አማራ ህዝብ ሳይጮህ ሌሎች ነገዶችን መዉቀስ መራራ ቀልድ ነዉ::እንኳን ለሰላሳ አመታት የኢትዮጵያዊነት ቅድስና እና አንድነት በተዋረደበት ሁኔታ ብሎም ኢትዮጵያዊነት በጎሳ ፖለቲካ እንዲጠፋ በተደረገበት ሁኔታ አንዱ ነገድ ስለ ሌላዉ ነገድ ተነስቶ ካልጮህልኝ ብሎ መዉቀስ ከባድ እንዲሆን ተደርጓል:: ————– ማጠቃለያዉ ———– እናማ ማጠቃለያዉ አንድ ነዉ::በትግራይ እየተካሂያደ ላለዉ የጦርነት ተፈናቃዮች/ተጎጅዎች እርዳታ ሊያሰባስቡ አርቲስቶችን ማበረታታት እንጂ መዉቀስ አይገባም::ይልቅስ በስፋት በዳተኝነት በአያገባኝም ባይነት: በማይረባ ይሉኝታ እና በከንቱ ፍርሃት ለጥ ብሎ የተኛዉን እጅግ ብዙዉን አርቲስት በመላ ሀገሪቱ ተፈናቅሎ:ተገሎ እና የዘር ፍጅት እየተደረገበት ያለዉን የአማራ ህዝብ እንዲሁም የተዋህዶ እምነት ተከታዩን ህዝብ እንዲያግዝ/እንዲረዳ ጨቅጭቁት: ቀስቅሱት ተችሁት ብሎም አበረታቱት:: ኢትዮጵያዊ ቅድስናችሁን አትርሱ::የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም እግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ያለዉ ህዝብ መሆኑን አትርሱ::የኢትዮጵያን ቅድስና በጎሳ ፖለቲካ ካንሰራማ አስተሳሰብ ያቆሸሹትን ሁሉ እግዚአብሄር ከስራቸዉ ነቅሎ እንዲያጠፋቸዉም ጸልዩ:: ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Mekuria

    በጀቡብ ከልል፣ ቤኒሻንጉል ኦሮሚያ በመቶ ሺዎች ሰሞኑን ተፈናቅለዋል። አለም አቀፍ ወይም ያገር ውጥ ርዳታ አላገኙም። ከትግራይ ወደ ሱዳን ለተፈናቀሉ ከውጪ ርዳታ እየጎረፈ ነው። አርቲስቶቻችን እኪ ለአገር ውስጥ ቅድሚያ ስጡ።

Leave a Reply