በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል

በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ22 አመት ወጣት ሲሆን ፈይሳ ተካ ይባላል፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡

ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት ለኦነግ ሰራዊትነት ተመልምሎ ጊንጪ አካባቢ ጭልሞ በምትባል ቦታ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ26 ባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡

ከስልጠና በኋላም ሁሉም ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱና ስልክ ሲደወልላቸው የሚፈለጉበት ቦታ ድረስ እንዲመጡ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ወጣቱ ከኢፕድ ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል፡፡

እንደተባለውም የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ማንነቱን በማያውቀው ሰው አማካኝነት ስልክ ተደወለለት፡፡

በተባለው ቦታ ተሰባሰቡና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ አደረጉ፤ በእግርም በተሸካርካሪም ከተጓዙ በኋላ ጨርጨር አካባቢ ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቀሉ፡፡

ፈይሳ ተካ ስም ተቀየረለትና የትግል ስሙ ብሩክ ተካ ሆነ ፡፡ ምግብና ትጥቅ ተሟላላቸው፤ በወር ከስድስት ሺህ እስከ ሰባት ሺህ ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሯቸው ወደጥቃት እንዲገባ ስምሪት ተሰጠው፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርና እርሱ ግን አለመሳተፉን ይናገራል፡፡ አመራሮች የትግሉ ዓላማ ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት እንደሆነ ይነግሯቸው እንደነበርም ይገልጻል፡፡

ቃል የተገባላቸውን የወር ደመወዝ ሲጠይቁ ግን መንግስት የኢኮኖሚ ምንጮችን ስለዘጋብን መክፍል አንችልም የሚል መልስ እንደተሰጣቸውም ነው የተናገረው፡፡

መከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር እርምጃ ሲጀምር ፈይሳ እጁን በሰላማዊ መንገድ ሰጥቷል፡፡

በማያውቀው ነገር በሰዎች ተታሎ በጥፋት ዓላማ ውስጥ መሳተፉ እንደጸጸተው ፈይሳ ገልጾልናል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply