በትግራይ ክልል ህጻናት እና ሴቶችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እና ጾታዊ ጥቃት ተባብሷል ተባለ። የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ ካልአዩ መሐሪ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ካለፉት ጥ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/oHtEmnbZv2LwBzi0k7FL55cGhMwPlqy6LCaLxUeIr_7lRzdYLCoRh269kyhq-iOuFNb-JgXjL0gsEArGGGgs-qZ9c6MvPt3UIIM21k08W2WVNao6YZr8QdkJoVBLt0FXzw1M__5IsSTEWO6TUtZaErzsIf6BkK2vLLAeV_LuZtaSTANvkyee0gHke23pWmexkmRzrau6Amga5_XvcIujafOdyekHzKuQaPUFUIgKutzOObVMTYnBB1jyiWoKbdngPTutG_4hOWvB-wN7zOdsJdeMW0SYm-_woh-XSbIvCTdAi2OJ8m-Fg-nWm0KUmksCPIZYJJ2CJlLhE0IVEC2K3Q.jpg

በትግራይ ክልል ህጻናት እና ሴቶችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እና ጾታዊ ጥቃት ተባብሷል ተባለ።

የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ ካልአዩ መሐሪ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በክልሉ ህጻናት እና ሴቶችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ እና ጾታዊ ጥቃት ተባብሷል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በሚገባ እያወቀ ለመከላከል ግን ዳተኝነት እንደሚታይበት የሚናገሩት ፀሀፊው፤

በክልሉ ለሚታየው የሴቶች እና ህፃናት መደፈር እና እገታ እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት ትጥቅ ያልፈቱ ታጣቂዎች ተባባሪ እንደሆኑም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል የበርካታ አካላት ተሳትፎ ያለበት የተደራጀ የመሬት ወረራ መኖሩን አስታውቆ የነበረው ፓርቲው ገዳዩ ከመቀነስ ይልቅ በከፍተኛ ሁኔታ የመጨመር አዝማሚያ እየታየ እንደሆነም ገልጸዋል።

የመሬት ወረራው በተደራጀ መንገድ እየተካሄደ የሚገኘው በመቀሌ ዙሪያ፣ሰብዓ እንደርታ እና በተለያዩ የገጠር ወረዳዎች ሲሆን በ ዘና እና ሽሬ አካባቢዎች ደግሞ የማዕድናት ስርቆት በስፋት እንደሚታይ አንስተዋል።

በለዓለም አሰፋ

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply