በትግራይ ክልል ለስደተኞች የምግብ አቅርቦት ሊጀመር ነው ተባለ

በክልሉ  ለሚገኙ ከ25 ሺ በላይ የኤርትራ ስደተኞች ተቋርጦ የነበረዉ የምግብ እና ተያያዥ ግብአቶች አቅርቦት ካሳለፍነዉ ሳምንት ጀምሮ መቀጠሉን የስደትና ስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

በህግ ማሰከበር ዘመቻዉ ወቅት ለኤርትራ ስደተኞች ተቋርጦ የነበረው የምግብ እና ተያያዥ ግብዓቶች እደላ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምር ዳግም መጀመሩን የኤጀንሲው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክተር አቶ በአካል ንጉሴ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ከ25 ሺ በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች እደላው መከናወኑንም ተናግረዋል፡፡

በአካባቢዉ 4 የሚሆኑ ካምፖች መኖራቸውን የነገሩን ሲሆን ሁለቱ ግብአቶችን ባሟላ መልኩ የተደጁ መሆናቸውን ጠቅሰው የተቀሩት ሁለቱ በርካታ ጉድለቶች ያሉባቸዉ ከመሆኑ አንጻር የማሸጋሸግ ስራዎች በተከወኑበት ወቅት ኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞችን እያስወጣች ነዉ የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች መናፈሳቸውን እና ፍጹም የተሳሳተ መረጃ ነዉ በማለትም ገልጸዋል፡፡

በህግ ማሰከበሩ ዘመቻ ወቅት የህወሓት ቡድን ማሰተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ላይ ዘረፋዎችን እና ጥቃቶችን ፈጽሟል ሰራተኞቻችንም ከስራ መፈናቀል እና እስርም ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

********************************************************************************

ዘጋቢ፡ቤዛዊት ግርማ

ቀን 21/04/2013

አሀዱ ራዲዩ 94.3

ምስል፡- የተቋሙ መረጃ

Source: Link to the Post

Leave a Reply