በትግራይ ክልል ውስጥ ከጳጉሜ 2 ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መታገዱ ተገለጸ፡፡
በክልሉ ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ያለመ ነው የተባለው ይኸው ሰላማዊ ሰልፍ፤ በውናት፣ ሳልሳይ ወያነና ባይቶና ትግራይ ፓርቲ አማካኝነት መጠራቱ የተነገረ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉ በአዲሱ የመቀሌ ከተማ አስተዳደር መታገዱ ታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ትናንት ለሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆች በላከው ደብዳቤ፤ የከተማ አስተዳደሩ ለሰላማዊ ሰልፍ የፀጥታ ጥበቃ ማድረግ እንደማይችል ነው ያሳወቀው፡፡
የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄው ህገመንግስታዊ ነው ያለው የከተማ አስተዳደሩ፤ ደብዳቤ ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራበት ወቅት የበዓል ዋዜማ በመሆኑና ግርግር የሚበዛበት ወቅት በመሆኑ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ሊያውክ ስለሚችልና ለሰላማዊ ሰልፍ በቂ የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ ሰልፉ ሊካሄድ አይችልም ብሏል፡፡
Source: Link to the Post