በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በ11 ወራት ውስጥ 12 ሴቶች ሲገደሉ 178 የግድያ ሙከራዎች መፈጸማቸውን ፖሊስ አስታወቀ 

ቅዳሜ ሰኔ22 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ባለፉት 11 ወራት ውስጥ በከተማው 12 ሴቶች ተገድለው በድምሩ ከ4 ሺህ በላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል አለ።

አዲስ ማለዳ ከክልሉ መገናኛ ብዙኀን እንደተመለከተችው ከሰሞኑን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የነበረው መረጃ የ11 ወራት ሪፖርት መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በ2016 ባለፉት 11 ወራት 4 ሺህ 340 ወንጀሎች የተመዘገቡ ሲሆን ወንጀሎቹ 7 ዓይነት ናቸው። 12 ሴቶች ሲገደሉ፣ 80 የአስገድዶ መደፈር፣ 1 ሺህ 953 የስርቆት፣ 583 የድብደባ፣ 178 የግድያ ሙከራ እንዲሁም 10 የጠለፋ ወንጀሎች መሆናቸውን የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ገልጿል።

ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ170 በላይ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሃይሎችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ በእጅጉ ያስፈልጋል ተብሏል።

በቅርቡ በክልሉ ዋና ከተማ እና ሌሎችም አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና አፈና ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎች እንደተካሄዱ መዘገባችን አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply