በትግራይ ክልል ርሃብ አልተከሰተም ተብሎ የሚነሳው ሀሳብ አሳዝኖኛል ሲል-ባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ በትግራይ አልተከሰተም ተብሎ በመንግስት ደረጃ መ…

በትግራይ ክልል ርሃብ አልተከሰተም ተብሎ የሚነሳው ሀሳብ አሳዝኖኛል ሲል-ባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ አስታወቀ፡፡

ባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ በትግራይ አልተከሰተም ተብሎ በመንግስት ደረጃ መግለጫ ማውጣት ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም ሲል ገልፃል፡፡

ይህንን የገለፁት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ በርሄ ከ ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡

በክልሉ የነበረውን ድርቅ እና ርሃብ በተመለከተ ከግዚያዊ መንግስቱ ቀድመን ጥናቶችን በማድረግ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደርግ ጠይቀን የነበረ ቢሆንም የሰማን አካል አልነበረም ብለዋል፡፡

ትግራይ ክልል ከጦርነት ጠባሳ ያልዳነ በመሆኑ እንዲሁም ከጦርነቱ በፊትም ሆነ በኃላ ከፍተኛ የሆነ የአንበጣ መንጋ ፈትኖት መቆየቱ ተናግረዋል፡፡

ከዛም በኃላ የዝናብ እጥረቱ የከሰተው ድርቅ ህዝቡ ምንም ማምረት እንዳይችል በማድረጉ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት ህዝቡ ብቻም ሳይሆን እንስሳትም ጭምር በገጠርም በከተማም በርሃብ ምክንያት እየሞቱ ይገኛል ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ይህ በሆነበት ሁኔታ ግን የፌደራል መንግስቱ በአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽኑም ሆነ በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል ርሃብ የለም ብሎ መግለጫ መስጠት ከጦርነት አዋጅ አይተናነስም ብለዋል፡፡

አሁን ያለው ችግር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ የሚፈልግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ዜጎች ለህዝቡ ሊደርሱለት ይገባል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ከ77ቱ ድርቅ የሚስተካከል ደርቅ ተከስቷል የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር ይሁን እንጂ የፌደራል መንግስት በኮሚኒኬሽኑ በኩል ባወጣው መግለጫ ርሃብ አልተከሰተም ሲል አስተባብሏል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply