በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማምጣት መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማምጣት መንግሥት ሁልጊዜም ቁርጠኛ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትግራይ ክልል የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። የዛሬው ውይይትም በክልሉ ሰላም እና ልማትን ለማምጣት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት። ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply