You are currently viewing በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ወላጆች ቅሬታ አሰሙ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም…

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ወላጆች ቅሬታ አሰሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም…

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ወላጆች ቅሬታ አሰሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዛሬው ዕለት ከ200 በላይ የሚገመቱ ወላጆች አዲስ አበባ በሚገኘው የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደጃፍ ላይ በመገኘት ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ ለቅሬታ ወደ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያመሩት ወላጆች ልጆቻቸውን በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ ናቸው ተብሏል፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከመካከላቸው 10 ተወካዮችን በመምረጥ ወደ ወደ ሚኒስቴር ቢሮው መፍትሔ ለመጠየቅ መግባታቸውን አዲስ ዘይቤ በስፍራው ከሚገኙ ወላጆች በስልክ ሰምታለች፡፡ ዓላማቸው ‹‹ልጆቻችን አሁን ስላሉበት ሁኔታ የምናውቅበት መንገድ ይመቻች›› የሚል ሐሳባቸውን ለሚመለከተው አካል ማሰማት መሆኑን የሚናገሩት ተሰብሳቢዎቹ የፌደራል መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ልጆቻቸውን ሁኔታ ማወቅ አለመቻላቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ፡፡ ከቅሬታ አሰሚዎቹ መካከል ስማቸው በዚህ ዜና ላይ እንዲጠቀስ ያልፈለጉት ወይዘሮ ‹‹ልጆቻችን አሁን ስለሚኙበት ሁኔታ ምንም የምናውቀው ነበር የለም፡፡ መንግሥት ኃላፊነት ተሰምቶት መራጃውን የምናገኝበትን መንገድ ሊያመቻችልን ይገባል፡፡ የተቋረጠው የስልክ አገልግሎት ተመልሶ ወይም የትራንስፖርት ሁኔታዎች ተመቻችተው ልጆቻችንን እንድናገኝ መንግሥት ይርዳን›› ብለዋል፡፡ አዲስ ዘይቤ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply