በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖች በግጭት ምክንያት የተጎዱ የውሃ አውታሮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለጸ

ሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የውሃ አውታሮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው አስታወቀ።

የውሃ አውታሮቹን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የውሃ ፓምፖች፣ ጄኔሬተሮች እና የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎችን በመለገስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረጉን ኮሚቴው በይፋዊ የትስስር ገፁ ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply