በትግራይ ክልል በዝናብ እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱ ተገለፀ፡፡በሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞን የተወሰነ ዝናብ ቢኖርም በደቡብ፣በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከፍተኛ የዝናብ እጥ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/XDarPV3ymOvCe9R-Z8QNykQAzsj4MGHq5HWGTDCAvEjBzfPga5GPFzZewTzFw1AHHQZqm0hmtQKBLf2zQhEt9QfjL-JqDyA_r-doAZW643w4E2MYLO9NFW-QvYxxy4Zz1H8itkz-6lkeKdpQpCWAdZgzTFSKyqEqVwyRXof1TDDXaTRNDHfoJfeRs5FGUowyaRXBw49cAuf8T5FxdU6JtH6mr73BcE878JJ5uku_9lTMOjJav7S_pE5JBUzuSJvOlgXKVk9C_D_LdmUp4K93OfWRJ58NQZLk-S4fvx63G-nnPIo0uJf4yh7YjV9Nam1eQJD10jfEDcr7UwgOWsSiNA.jpg

በትግራይ ክልል በዝናብ እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱ ተገለፀ፡፡

በሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞን የተወሰነ ዝናብ ቢኖርም በደቡብ፣በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከፍተኛ የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ ድርቅ ሊከሰት እንደቻለ ተገልፃል፡፡
በአሁን ሰዓት የበቀለ ምንም ዓይነት እህል የለም የበቀለውም በሙሉ ወድሟል ሲሉ የትግራይ ክልል ግዚያዊ መስተዳድር የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ቅድ፣ ማስጠንቀቂያና ግብረመልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረእግዚአብሄር አረጋዊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በኢሮብ፣የእንደርታ ወረዳዎች ፣ራያ አዘቦ እና ጨርጨር ከፍተኛ የሆነ ድርቅ የተከሰተባቸው አከባቢዎች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይም ተዘርቶ የነበረው ማሽላ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ነግረውናል፡፡
ከድርቁ ባሻገር በክልሉ የተከሰተው የዛፍ ላይ አንበጣና ተባዮች በሰብል ላይ እያሳደሩ የሚገኙት ጉዳት ያለውን ችግር እንዳባባሱት አስታውቀዋል፡፡

የድርቅ ሁኔታውን ለመከላከል ከወረዳ እስከ ቀበሌ ውሃ የማቆር የተወሰነ ስራ እየተሰራ ቢሆንም የዝናብ እጥሩ በዚሁ ከቀጠለ የድርቁ ሁኔታ ከአቅም በላይ እንደሚሆን ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለውን ድርቅ መፍትሄ ለመስጠት ግብረሰናይ የረድኤት ተቋማት፣ፌደራል መንግስት እና የሀገረ ውስጥ ረጂ ተቋማትን ትብብር እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራ ክልል በዝናብ እጥረት ሳቢያ የተከሰተው ድርቅ በታህሳስ ወር የከፋ እንደሚሆን መገለፁ ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ
መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply