የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በወቅታዊ ጉዳይ እና በ2013 በሚካሄደዉን ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ነው፡፡
በመግለጫዉ ላይ የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት፣በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የሌላ ሀገር ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተ መንግስት ግልጽ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በክልሉ ተፈጽሟል የተባለዉ የንብረት ዘረፋና የሴቶች መደፈርን በተመለከተም በገለልተኛ አካል እንዲጣራ መደረግ እንዳለበት ኢዜማ ጠይቋል፡፡
መንግስት የዜጎችን ደህንነት ሊያረጋግጥ ይገባል ያለዉ ፓርቲዉ፣ በምዕራብ ወለጋ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የንጹሃን ግድያና መፈናቀልን በተመለከተ መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡
ከሁሉም በፊት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠዉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ከፍተኛ ፍይዳ እንዳለዉ እንደሚገነዘብ ኢዜማ ተናግሯል፡፡
ይሁንና አመራሮቻቸው በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው እና በመጪው ምርጫ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ ሲገልጹ መሰማቱ፣ በመጪው ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ኢዜማ ጠቁሟል፡፡
ኢዜማ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተከሰቱ ግጭቶች እና መፈናቀሎች የደረሰዉን የጉዳት መጠን የሚያጣራ ቡድን ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑንም አስታዉቋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
በዳንኤል መላኩ
ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም
Source: Link to the Post