በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በታቀደው መንገድ እየሄደ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በታቀደው መንገድ እየሄደ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ዘመቻው በክልሉ ተቀባይነት ያለው ህጋዊ አስተዳደር ሲመሰረት እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል፡፡በተያያዘም የአገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን መቆጣጠሩ ተሰምቷል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊት ህውሓት ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። ሰራዊቱ የህወሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት መልሶ በማጥቃት በአሁኑ ሰዓት ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት መረጃን ጠቅሶ ኢቢኮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply