በትግራይ ክልል ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

በትግራይ ክልል ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የትግራይ ክልል ህግ ማስከበር እና ህልውና ዘመቻ መጠናቀቅ ማግስት ዜጎችን በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች መድረስ ቀዳሚ ትኩረት በአብዛኛው በሀገሪቱ መንግስት ቀሪው ደግሞ በተርዓዶ ደርጅቶች መቀጠሉ ተገልጿል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የብሄራዊ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ÷ ከጣቢያችን ጋር የስልክ ቆይታ የነበራቸው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳም በጥቅሉ በትግራይ ክልል ብቻ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ለመድረስ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በቀጣይነትም እንደ ትግራይ ክልል እና ሀገር እየተደረገ ያለው ድጋፍ ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር 10 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ከውጭ እና ከሀገር ውስጥ ምርቶች ግዥ እየተፈጸመ ነው ብለዋል።
ሀገሪቱ ለአመታት ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም ያካበተችው ልምድ ሲታይ አሁን ላይ ያሉትን ችግሮች የመቋቋም ቁመና ላይ ናትም ነው ያሉት ።
መቀሌ የደረሰው ድጋፍ እስከ አድግራት እና አካባቢዎቹ ላሉ ነዋሪዎች የሚደርስ ሲሆን÷ሽሬ ላይ የደረሰውም ድጋፍ ቢሆን ከአክሱም እስከ አድዋ ብሎም ሽራሮን እና ሌሎችን አካባቢዎች ይደርሳል እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ።
ከዚያም ባለፈ አላማጣ የደረሰው ደግሞ ኮረም ፣ጨርጨር ፣ መሆኒ እናሌሎችም ጋር ለመድረስ እንደ መሰላል ያገለግላል ነው የተባለው።
ከተለያዩ ተቋማት ጋር ዜጎችን የመደገፍ ተግባር የሚፈጽመው ኮሚሽኑ የትግራይን ክልል ከፊት አመጣን እንጂ ከአንበጣ እስከ ጎርፍ ከዚያም ሲያልፍ በግጭት እና በሌሎች ምክንያቶች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት እና ለችግር እጅ ለሰጡት ዜጎች ድጋፉን መቀጠሉን አንስተዋል።
በዚህም ከአማራ እስከ አፋር ፣ ከቤንሻንጉል እስከ ሌሎችም ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
በሀገራችን በ2008 ኤልኒኖ ያስከለው ድርቅ 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎችን እጅ ለድጋፍ እንዲዘረጉ አድርጓቸዋል።
ይህ ደግሞ ባለፉት 50 ዓመታት የሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ያልተከሰተ እንግዳ ክስተት ነበር ነው ያሉት።
ይህም ሆኖ ግን አንድም ሰው ህይወቱ አላለፈም ነበር የሚሉት የብሄራዊ አደጋ ስጋትና አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ÷ ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም የሚከብድ ደረጃ ላይ የለንም ብለዋል።
በቀጣይነትም ከውጭ 10 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ እና ከሀገር ውስጥም የተለያዩ ምርቶችን ለመግዛት መንግስት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በትግራይ ክልል ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply