የትግራይ ክልልን ፖሊስ በአዲስ መልክ በመመልመል ስራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የፌዴራል ፖሊስ ያስታወቀው፡፡በትግራይ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መመለሳቸውን ተከትሎ የፖሊስ ሃይል ይደራጃል ሲል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የትግራይ ክልልን ፖሊስ በአዲስ መልክ በመመልመል ስራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የፌዴራል ፖሊስ ያስታወቀው፡፡
ህግን የማስከበሩ ስራ በመከላከያ እና በፌዴራል ፖሊስ እየተሰራ ቢሆንም አሁን ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሰላሙን ሂደት የሚመሩ የፖሊስ ሃይሎች ተመልምለው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጀላን አብዲ ለአሀዱ እንደተናገሩት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር የሀገር መከላከያ እና በፌዴራል ፖሊስ እየሰሩ ቢሆንም በክልሉ የፖሊስ ሰራዊት አስፈላጊ በመሆኑና በህብረተሰቡ ተገምግሞ ወደ ስራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በትግራይ ክልል በአሁኑ ሰዓት የክልሉ ፖሊስ ትጥቅ መፍታትን ተከትሎ የክልሉ ህግን የማስከበር ሂደቱ በመከላከያ ስር እንደወደቀ ይታወሳል፡፡
አዘጋጅ: አንዷለም ስማቸው
Source: Link to the Post