በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታን በሚያቀርቡ አለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ተጠያቂ አይደለሁም ማለቱ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት አስታወቀ፡፡

ጦርነት ሰብዓዊ ቀውስን የሚያስከትል እንዲሁም መሰረተ ልማትን የሚያወድም እንደመሆኑ የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉ የሚበረታታ መሆኑን ድርጅቱ ገልጻል፡፡የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየው ከትናት በስቲያ በአሀዱ ሬድዮ አሀዱ መናገሻ ፕሮግራም ላይ  በነበራቸው ቆይታ በየትኛውም ሀገር የሚደረጉ ጦርነቶች መጨረሻቸው በስምምነት የሚጠናቀቅ ሲሆን  የሚያስከትለው ጉዳት ግን  በብዙ ዓመት የማይከፈል እዳ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር መንግስት ተጠያቂ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በትግራይ ክልል ውስጥ ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ችግር መንግስት ተጠያቂ አይደለሁም ማለቱ ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉ የሚደገፍ ቢሆንም ህውሃት ድጋሚ እንዲያንሰራራ እድል የሚፈጥር እንዳይሆን ትኩረት እንዲሰጠውና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ አቅጣጫ ሊኖር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ እንደ ቀይመስቀል የመሳሰሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች ለሚያደርጉት የሰብዓዊ እርዳታ በሚፈጠረው ችግር  መንግስት አይመለከትኝም የሚል ከሆና እርዳታን ማድረስ የማይችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ስለሚችል አሳስቦኛል ብለዋል፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ እንደመሆኑ ጥፋተኞችንም ለህግ ማቅረብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ቀን 28/10/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply