በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ንፁሃንን ገሏል እየተባል የተናፈሰው መረጃ የሃሰት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ለአሐዱ እንደገለፁት የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ንፁሃን ዜጎችን ገድሏል እየተባለ የተናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ባካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ የህውሃትን ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰሱን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ አሁንም አንዳንድ የህውሃት አባላት የሽፍታነት ባህሪ በመላበስ በጫካ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ተናገረዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ስነ ምግባራ የተገነባ ህዝባዊ መሰረት ያለው የህዝብ ልጅ በመሆኑ እንዲዚህ አይነት ድርጊት እንደማይፈፅም ሜጀር ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡

ቀን 30/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ንፁሃንን ገሏል እየተባል የተናፈሰው መረጃ የሃሰት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply