በትግራይ ክልል የገጠር መሬት በከፍተኛ ሁኔታ እየተወረረ ነው ተባለ፡፡

በትግራይ ክልል ሰባ እንደርታ አከባቢዎች የመሬት ወረራ በተደራጀ መንገድ እየተካሄደ ነው ሲል ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ የክልሉን መንግስት መክሰሱን ሰምተናል፡፡

ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የፓርቲው ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ ካልዓዩ መሐሪ በመቀሌ ሰብዓ እንደርታዎች የመሬት ወረራ በተደራጀ መንገድ የገበሬውን መሬት የመውረር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ዋና ፀሀፊው የመሬት ወረራው በመላው ትግራይ አሳሳቢ ሆኗል ያሉ ሲሆን ነገር ግን በራያ እና በመቀሌ ሰብዓ እንደርታዎች ወይም በመቀሌ ዙሪያ ባሉ የገጠር አካባቢዎች የመሬት ወረራው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

ወረራውን እየፈፀመ የሚገኘው ደግሞ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደርና ባለሀብቶች በጋር በመሆን ነው ሲሉ ነው የሚከሱት፡፡

ወደከተማ ገብታቹሀል፣ለልማት ይፈለጋል እየተባለ የገበሬውን መሬት በግፍ ለባለሀብት እየሰጡት ነው ተብሏል፡፡

በመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ከ30 እና 40 ዓመት በላይ የገበሬው መሬት ሲወረር ነበር የተባለ ሲሆን ከሰሞኑ ግን በተባባሰ መልኩ ዘረፋ እየተፈፀመበት ነው ይላል ፓርቲው፡፡

ይህ ድርጊትም በአስቸኳይ እንዲቆም ሲል ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ አሳስቧል፡፡

አቤል ደጀኔ

ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply