የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ /ኢሰመጉ/ እየደረሱት ባለው መረጃ መሰረት የዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን መገንዘቡን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዳን ይርጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በተለይም በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ፃታዊ ጥቃት በአፋጣኝ መቆም ይገባዋል ነው ያሉት፡፡
በጦርነት ክፉኛ በተጎዳ ህዝብ ላይ ሌላ ቁስል እንደመጨመር ነው የሚሉት አቶ ዳን፣ የችግሩን መጠን ስር ሳይሰድ መፍትሄ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል ከጦርነት ማግስት በርካታ የተደራጁ ዘራፊዎች፣የታጠቁ ሀይሎች ሴቶችን መደፈር እንዲሁም በቡድን ዘረፋ እየፈፀሙ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በቅርቡም በመቀሌ ከተማ አሸንዳ ለማክበር የወጣችን እንስት በተደራጁ አካላት ህይወቷ እንዲያልፍ የተደረገ ሲሆን አንድ የቀድሞ ሠራዊት አባልም እንዲሁ በአንድ ምሽት ቤት የእጅ ቦንብ በመወርወር የአምስት ሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ማድረጉ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ይታወሳል፡፡
ይህንን ዓይነት ዘረፋና ግድያ መቀሌን ጨምሮ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የሚስተዋል በመሆኑ የሚመለከተው አካል በተለይም ግዚያዊ አስተዳደሩ የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ ይገባዋል ሲሉ የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳን ይርጋ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
በአቤል ደጀኔ
Source: Link to the Post