በትግራይ ክልል ደሞዛቸዉ የተቋረጠባቸዉን የግል ድርጅት ሰራተኞች ደሞዝ ለመክፈል አስቸጋሪ ሆኗል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ጉዳዩ ውስብስብ እንደሆነ አንስተው በጦርነት ውስጥ ያላመረተን ድርጅት ደሞዝ እንዲክፈሉ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንደሌለም ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ለ 2 ዓመት ምንም ደመወዝ ያላገኙ የግል ሰራተኞች ደሞዙን ሊያገኙ የሚችሉበት የመጨረሻ አማራጭ ሁለቱም አካል በሚያድርጉት ውይይት ብቻ እንደሆነ ተነስቷል፡፡

አቶ ካሳሁን ምንም እንኳ በክልሉ ከጦርነቱ በኋላ ዳግም ስራ የጀመሩ ቢኖሩም እስካሁን ስራ ያልጀመሩ ድርጅቶች በመኖራቸው ሰራተኞቹ በችግር ውስጥ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

የሰራተኞቹ ችግር ለማቃለል ልዩ ውይይት ያስፈልጋል ለዚህም በመቀሌ የሚገኘው ቅርንጫፋችን ስራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል።

በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የድርጅት ትርፋማነትን ታሳቢ አድርጎ ለሰራኞች ደመወዝ እንደሚከፈል ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ሰራተኞቹ ደመወዝ ያልተከፈላቸው መቼ እና ድርጅቱ በምን አይነት ሁኔታ ዉስጥ እያለ ነው የሚለው ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነውም ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ያሉ የመንግስት ሰራተኞችና ጡረተኞች ጉዳይ መንግስት በፖለቲካዊ ውሳኔ ደመወዛቸውን ለመክፈል መወሰኑን ጣቢያችን መዘገቡ ይታወሳል።

በለአለም አሰፋ

ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply