በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የፌደሬሽን ምክር ቤት ወስኗል።       አሻራ ሚዲያ    ጥቅምት 28 /2013 ዓም ባህር ዳር በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜ…

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የፌደሬሽን ምክር ቤት ወስኗል። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 28 /2013 ዓም ባህር ዳር በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜ…

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የፌደሬሽን ምክር ቤት ወስኗል። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 28 /2013 ዓም ባህር ዳር በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የሕዝቡን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር እንደሚሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ ገለፁ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔውን አስመልክቶም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አደም ፋራህ እንዳሉት “የሚቋቋመው አስተዳደር በሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መሰረት የሚሠራና የትግራይን ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚያስከብር ይሆናል” ብለዋል። “ሕገወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚከበረው በእሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል” ብለዋል። ይህም የሕገ መንግስቱን መርሆዎች የሚፃረር እንደሆነ ነው የገለጹት። ሕገወጥ ቡድኑ የፌዴሬሽንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ውሳኔዎችን በመጣስ ኢ-ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ በሃገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱንም አስታውሰዋል። በመሆኑም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቡድኑ ወደ ሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ የተለያዩ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ የቆየ ቢሆንም ሊቀበል ባለመቻሉ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ፣ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋምና የፌዴራል የፀጥታ አካል በክልሉ እንዲሰማራ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል። በትግራይ ክልል የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በአጭር ጊዜ የሚቋቋም ሲሆን ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግስት ይሆናል ተብሏል። የሚቋቋመው አስተዳደር የክልሉ ምክር ቤትና ካቢኔ ሲሰራቸው የነበሩ ተግባራትን እንደሚያከናውንም ተገልጿል፤ኃላፊነቱን ለመወጣትም እስከታችኛው መዋቅር ድረስ አስፈፃሚዎችን የሚመድብ ይሆናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply