በትግራይ ክልል ግብርና ለማስጀመር ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ እንዳሉት በትግራይ ክልል 70 በመቶ ግብርና ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል ።

ይህም 1.2 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ወደ ግብርና ሥራቸው እንዲመለሱ ያደርጋል ነው ያሉት።

በትግራይ ክልል ስላለው ነባራዊ ሁኔታ በሚመለከት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሳሳተ መረጃን ያሰራጫል ያሉት አምባሳደር ዲና በመጪው ክረምት በትግራይ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ወደ ግብርና ስራቸው ይመለሳሉ ብለዋል።

ለዚህም ማዳበሪያና የዘር አቅርቦት እንደሚቀርብላቸው ተገልጿል።

ከግብርናው በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ ፋብሪካዎች በተለይም የጨርቃጨርቅና ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል ተብሏል ።

በግጭቱ ምክንያት የወደሙትን መሠረት ልማቶች የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ያነሱት ቃል አቀባዩ በቅርቡ የባንክ፣ የቴሌና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ ሙሉ በሙሉ ለማስጀመር እየሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሽሬና የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ወደ ስራ የማስገባቱ ስራ እንደሚከናወንም ተነስቷል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 03 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply