በትግራይ ወራሪ ቡድኖች ባለፉት አምስት እና ስድስት ወራት የተፈጸመበት ግፍ ሳይወድ በግድ የወልድያና አካባቢው ህዝብ የዕድሜ ጣራ ካልገደበው በስተቀር ሁሉም የውትድርና ስልጠና እንዲወስድ እ…

በትግራይ ወራሪ ቡድኖች ባለፉት አምስት እና ስድስት ወራት የተፈጸመበት ግፍ ሳይወድ በግድ የወልድያና አካባቢው ህዝብ የዕድሜ ጣራ ካልገደበው በስተቀር ሁሉም የውትድርና ስልጠና እንዲወስድ እየተገደደ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የወልድያ ኮሚዩኒኬሽን የፋኖዎችን ስልጠና እና ምርቃት አስመልክቶ “ግፍ ሲበዛበት ሽማግሌም ሾተል ይመዛል!” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ጽሁፍ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል:_ “ወሎ ገራገሩ”፥ ፍቅርን ሰጥቶ ፍቅርን መቀበል መለያ እሴቱ የሆነው የኢትዮጵያነት መገለጫ ጎልቶ ከሚታይባቸው የሀገራችን አካባቢዎች አንዱ ነው ወሎ። የጥንቱ ወሎ ክፍለ-ሀገር የዛሬው ለሕዝብ አገልግሎት ተደራሽነት ሰሜን እና ደቡብ ተብሎ ቢከፈልም ገራገርነቱ፣ ተግባቢነቱ፣ የሀገራዊ ፍቅሩ፣ የአንድነት ወኔና ስሜቱ ዛሬም ትኩስ ነው አልበረደም። ይህ ባህሪው የተዋሰው ወይም የቀላወጠው አይደልም ከአባቶቹ የወረሰው እንጅ። ህንጻን ከወደ ጥራና ጀምሮ መሠረት ላይ የመፈጸም ብቃት ባለቤት ከቅዱስ ላሊበላ እስከ መምህር አካለ ወልድ፤ ከሼህ ዑመር እስከ መጭው ጊዜና ክስተትን በስነ ቃል ቀማሪው ሼህ ሁሴን ጅብሪል ሀገር መገንባትን፣ መቻቻልን አብሮነትን ከሚዳሰስ ቅርስ እስከ ማይዳሰስ ባህላዊና ትውፊታዊ እሴት ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ከአባቶቹ ተቀብሏል። ይህ ገራገር ህዝብ ባለከራማው ሼህ ሁሴን ጅብሬል፦”ከተፈሪ፡ ወድህ፥ አይባልም፡ ራስ፡ አይባልም፡ አጤ፤ ሀገሩ፡ ይመራል፥ በመንደር፡ ወጠጤ።” ከሚለው አባባል በህውሃት መራሹ ኢህአደጋዊ ስርዓት ከደንበሩ እስከ ህይወቱ በወጠጤዎች ብቻ ሳይሆን፣ በጠቦቶችና ግልገሎች ግፍ የተፈጸመበት ሕዝብ ነው። ከውሎ አንዱ ክፍል በሆነው የሰሜን ወሎ የየጁ እምብርት “የጁ የእግዜር መሐል እጁ” በመባል በምትታወቀው ወልድያም በመንግሥታዊ ስርዓቱ ስም ከተፈጸመበት ረዝም ስልታዊ የሰቆቃ የግፍ ጊዜ ይልቅ ከስልጣናቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከባህልና እምነታቸው፤ ከኢትዮጵያዊነትና ከአእምሯቸው በተፈናቀሉ በትግራይ ወራሪ ቡድኖች በዚህ አምስት ስድስት ወራት የተፈጸመበት ግፍ ሳይወድ በግድ የአካላዊ እንዲሁም ዝቅተኛውና ከፍተኛው የዕድሜ ጣራ ካልገደበው በስተቀር ሁሉም ውትድርና ስልጠና እንዲወስድ አስገድዶታል። የወልድያ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ ለበቀል ሳይሆን፣ በህልውናው ላይ ለመጣበት አደጋ እንደ አባቶቹ መክቶ ለመምታት፣ ዳግም እህት እናቶቹ እንዳይደፈሩ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማቱ ለዳግም ውድመትና ምዝበራ እንዳይዳረጉ፤ ለፋኖው፣ ለልዩ ኃይሉ፣ ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ ተጨማሪ ደጀን በጭንቅ ጊዜ ከጎኑ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ሁለተኛው ዙር ሰልጣኝ ነፍጠኛው አማራ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪካዊ የባንዶች መሸማቀቂያ የአርበኞች መኩሪያ ወር ላይ ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቋል። ግፍ ሲበዛበት ሽማግሌም ሾተል ይመዛል። የዕለቱ መልዕክታችን ነው። ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply