በትግራይ የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች በተመድ መ/ቤት ፊትለፊት ተቃውሞ አሰሙ አሥራት ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም ልጆቻቸውን ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች…

በትግራይ የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች በተመድ መ/ቤት ፊትለፊት ተቃውሞ አሰሙ አሥራት ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም ልጆቻቸውን ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች እንዲሁም ቤተሰቦች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት – UN (አዲስ አበባ) ቢሮ ፊት ለፊት በአሁን ሰዓት ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ወላጆች እና ቤተስቦች ለትምህርት የላኳቸው ልጆቻቸው እንዲመለሱላቸው አጥብቀው እየጠየቁ ናቸው። ጁንታው ካለበት የሥልጣን ጥማትና ነፍሰ-በላነት የመነጨው የትግራይ ክልል ቀውስ ጋር ተያይዞበክልሉ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ለከፋ እንግልት ተዳርገዋል። ትላንት ሐምሌ 15 የመቀሌ ዩኒሸርሲቲ ባወጣው መግለጫ ፣ የፌደራል መንግስት እስከመጭው ማክሰኞ በጀት የማይልክልኝ ከሆነ ከ7500 በላይ ተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው ችግር ተጠያቂ አይደለሁም ማለቱ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply