በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና የለም ሲሉ ተናግረዋል።

ክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ በተጎዳበትና ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ በርካታ ቦታዎች በወራሪ ሀይሎች በተያዙበት ሁኔታ፣ ምርጫ ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ክልሉን እየመራ የሚገኘዉ ግዚያዉ አስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁነት የለዉም የሚሉት የዉድብ ናፅነት ትግራይ ዉናት ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቦ፣ አስተዳደሩ ወደ ምርጫ ገብቶ ለዉጥ እንዲመጣ ፍላጎትም ዝግጁነትም የለዉም ብለዋል።

በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ ቅርርብ መኖሩን የሚናገሩት የዓረና ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አንዶም ገ/ስላሴ ፣ በሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ውድብ ናፅነት ትግራይ እና ባይቶና አባይ ትግራይ ጥምረት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አረናም ጥሩ መቀራረብ ስላለዉ ምን አልባት መልካም ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫ ከተካሄደ በጋራ ለመወዳደር ዉይይት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ዓመት በ2016 ምርጫ ከሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች አንደኛዉ የትግራይ ክልል መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።
የትግራይ ክልልን ጨምሮ የስድስተኛው ዙር ቀሪ ምርጫዎችን በተለያዩ ጊዜያት ለማከናወን ዝርዝር ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳቀረበም አስታውቋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply