በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ሕገ ወጥ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ ማረጋገጡን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡
ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ ጽ/ቤቱ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡
*************************
ህዳር 09/2013
Source: Link to the Post