በትግራይ የሚገኙ ዜጎች ተመልሰዉ በእግራቸዉ እንዲቆሙ ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ዓለምዓቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ገለጸ፡፡

ከዚህ በላይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤በተጨማሪም የሚወዷቸዉን ላጡ እና ለመትረፍ እየተፍጨረጨሩ ያሉ የትግራይ ዜጎች ለጥያቄዎቻቸዉ ምላሽ ማግኘት አለባቸዉ ሲሉ የቀይ መስቀል የጥበቃ እና መሰረታዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ሳራ ኖትዝሊ በትግራይ በነበራቸዉ ጉብኝት ወቅት ገልጸዋል፡፡

አሁን የምገኘዉ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ነዉ ፤ በዚህ ያለዉ ሁኔታ እጅግ ልብ ሰባሪ ነዉ፡፡ ትግራይ በትጥቅ ግጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶባታል ፡፡ በዚህ ያለዉ ሁኔታም በጣም ልብ ሰባሪ ነዉ ሲሉ ነዉ የገለጹት፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ዜጎች ድጋሚ በእግራቸዉ ለመቆም ያላቸዉ ቁርጠኝነት እጅግ የሚያስደንቅ ነዉ ፡፡ ለዚህ ደግሞ ድጋፍን ይፈልጋሉ ነዉ ያሉት፡፡

እንደ ዓለምዓቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የምንችለዉን ሁሉ ድጋፍ እያደረግን ነዉ ብለዋል፡፡

ነገርግን ከዚህ በላይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ድጋሚ በሁለት እግራቸዉ ለመቆም እና ለጥያቄዎቻቸዉም ምላሽን ለማግኘት ይፈልጋሉ ስለዚህ ድጋፍ የግድ ነዉ ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀስን ነዉ፡፡ ድጋፍ ማድረጋችንንም ደግሞ እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply